ይህ የተገለፀው የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ በስሩ ካሉ የጤና ተቋማት ጋር የ2013 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ላይ ሲሆን ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሐረማያ ዪኒቨርስቲ በተካሄደው የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ እንደ ተናገሩት በ2013 በጀት አመት የእናቶችና የጨቅላ ህፃናት ሞት፣ ተላላፊ የሆኑ በሽታዋችንና ኤች አይ ቪ ኤድስን መከላከል እንዲሁም በስርአተ ምግብ እቅድ አፈፃፀም የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ገልፀዋል።
የቢሮ ኃላፊዋ አክለውም በ2014 በጀት አመት በዘንድሮ አመት ውጤት ያላስመዘገብንባቸወን በቀጣይ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ የሁሉም ሴክተሮች እርብርብ ይጠይቃል ብለዋል።
በጤና ቢሮ የእቅድ ክትትልና ግምገማ ዳሬክተር አቶ አለማየሁ ግርማ በበጀት አመቱ በእቅድ ክንውን ወቅት የገጠሟቸውን ተግዳሮቶች ሲገልፁ የኮቪድ ወረርሽኝ በመከሰቱ በመደበኛ ስራዋች ላይ ክፍተት መፍጠሩ አንዱና ዋንኛ ተግዳሮቶች ሆነውብናል በማለት ከበጀት እጥረት ጋር ተያይዞም የክትትልና ድጋፍ ስራዋችን ለማከናወን ምክንያት ሆኖብናል ብለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ አቶ አለማየሁ ሲገልፁ የረዥም ጊዜ የቤተሰብ እቅድ ተጠቃሚዋች የገጠሩ ማህበረሰብ መሆኑን ጠቁመው የከተማ ነዋሪዋች ይህን አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ መስራት ይኖርብናል ብለዋል።
በዕቅድ ግምገማ መድረኩ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ላይና በህፃናት ጤና ላይ በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ምሁራን የተሰሩ ጥናታዊ ፀሁፎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።
በጤናው ዘርፍ እየተገኙ ያሉ ውጤቶችን ለማጎልበት የህብረተሰቡንና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተጠቆመ።


