መምህር ስለሺ ካሳዬ ከአባታቸው ካሳዬ ወ/ሚካኤል እና ከእናታቸው ወ/ሮ ፈለቀች ደበበ ህዳር 12/1931 ዓ.ም በጉርጉሱም አውራጃ ፈናን ቢራ ከተማ ተወለዱ ።
መምህር ስለሺ ባለትዳርና የአራት ወንድ ልጆችና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበሩ ።
በ2010 በአገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደው በበጎ ሰው ሽልማት በመምህርነት ዘርፍ ተሸላሚ መሆን ችለዋል ።
የድሬደዋ አስተደደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሰራተኞች እና አመራር የተሰማንን ልባዊ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንመኛለን ።


