ኢኒፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ለታክስ አሰባሰብ ስረአቱ ውጤታማነት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ ::

    በአስታዳደራችን የገቢ አሰባሰብ ሂደቱን በዘመናዊ አስራር ለማጎልበት የሚያስችል 2.5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የዳታ ሴንተር ግንባታ እና የሶፍት ዌር ልማት ፕሮጀክት ተጠናቆ ተመርቋል።
    አቶ አብዱሰላም መሃመድ የድሬደዋ የገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ገቢ ለሁሉም ልማት ወሳኝ መሆኑን ገልፀው በተቋሙ የሚከናወኑ ተግባራ መረጃዎችን በአግባቡ በመያዝና አሰራርን የተቀላጠፈ ለማድር እንዲሁም የገንዘብ እና የጊዜ ብክነት ለመከላከል ግንባታው ተጠናቆ ወደተግባር የገባው ይህ ፕሮጀክት ወሳኝ ሚና አንደሚኖረው ተናግረዋል።ፕሮጀክቱ የተቋሙን ደህንነት ለማስጠበቅ እንደሚያስችል ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
    በፕሮጀክት ምርቃቱ ተገኝተው መልዕክት እና የስራ መመሪያ ያስተላለፉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኋላፊ አቶ ከድር ጁሃር ዘርፉን ወቀቱ በሚጠይቀው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማጎልበት የአስተዳደሩ ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ገቢ በሙሉ አቅም ለመሰብሰብ አንደሚረዳ ተናግረዋል።
    የታክስ መርጃእና ኒነፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ጥግነህ በድሬደዋ ተቋሙ አሰራሩን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የተለያዩ አመርቂ ተግባራት መከናወናቸውን አመልክተዋል።
    ፕሮጀክቱ ሪከርድ እና ማህደር ፣የንብረት አስተዳደር እንዲሁም የሰው ሃብት አስተዳደርን ጨምሮ የእቅድና በጀት ልማት ዘርፎችን ከወረቀት በፀዳ መንገድ በዘመናዊ አሰራር ለማከናወን እንደሚያስችል ለማወቅ ተችሏል