የአለም አቀፍ የቱሪዝም ቀንን በማስመልከት “ቱሪዝም ለሁለንተናዊ እድገት”በሚል መሪ ቃል ከመስከረም 4/2014ዓ/ም ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ ይከበራል::
የድሬዳዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙራድ በደዊ በሰጡት ማብራሪያ የአለም የቱሪዝም ጅርጅት አማካይነት በየዓመቱ መስከረም 17 ቀን በተለያዩ መሪ ቃሎች ሲከበር የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለዘርፉ ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግ ነው ብለዋል:
“ዘንድሮም ቱሪዝም ለሁለንተናዊ እድገት” ወይንም “Tourism for Inclusive Growth” በሚል መሪ ቃል ሲከበር ዘርፉ በኮቪድ 19 ከደረሰበት ጉዳት ለማነቃቃት ነው::
በመሆኑም ድሬዳዋችንም የወረርሽኙ ሰለባ በመሆኗ የቱሪስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የኮቪድ ፕሮቶኮልን በጠበቀ መልኩ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ በመሆኑ የሀገር ውስጥም ሆኘ የአለምአቀፉ ማህበረሰብ ከአመሰራረቷ ጀምሮ የአለም አቀፍ ፕሮቶኮል ጠብቃ የተመሰረተች የበርካታ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ መስህቦች ቅርስና ባህል መገኛ ወደ ሆነችው የፍቅርና የሰላም ከተማ ድሬዳዋ እንዲመጡ ግንዛቤ ለመፍጠርና የሀገር ውስጥ ቱሪም በማበረታት ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥቅም ለማሳደግና ለማነቃቃት ነው ብለዋል::
በፕሮግራሙ ከተሰናዱት ተግባራት ውስጥ
1. መስከረም 4 / 2014 ከጠዋቱ 12:30 ጀምሮ
የድሬዳዋ ኪነጥበብ ባለሙያዎችን ያሳተፈ
የጽዳት ዘመቻና ችግኝ ተከላ መርሃግብር
2. መስከረም 4/2014 ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ብስክሌት ግልቢያ
3. መስከረም 5 /2014 ጠዋት ከ2:30 ጀምሮ በድሬዳዋ ውስጥ የሚገኙ የቱሪስ አገልግሎት ሠጪ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ማላቅ ላይ ትኩረት ያደረገ የፓናል ውይይት እና የኪነጥበብ ምሽት
4. የከተማ ውስጥ የመስህብ ጉብኝት እና የባቡር ሽርሽር ፕሮግራም እንደሚካሄድ የተገለፀ ሲሆን በፕሮግራሙ መጨረሻ ላይ የምስጋናና የእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር የሚከናወን ይሆናል።
የድሬዳዋ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት
መስከረም 4/2014ዓ.ም


