በቀበሌው 09 አነስተኛ ድልድይ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።

    ፕሮጀክቶችን መጀመር ብቻ ሳይሆን አጠናቀው ለህዝቡ ማስረከብ እንደሚገባ የቀበሌ 09 አስተዳደር ገለፀ።
    በቀበሌው 09 አነስተኛ ድልድይ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ። በ2013 በጀት አመት በቀበሌው በአካባቢ ልማት ሊሰሩ ከታቀዱት ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው እና 1.2 ሚሊየን ብር ገደማ በፈጀው ድልድይ የምርቃት ስነ ስርአት ላይ የከንቲባ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፉአድ ሱጌ፣ የድሬዳዋ ትራንስፖርት ቢሮ ሃለፊ ወ/ሮ ሰአዲያ አዋሌና የቀበሌው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሀሰን ኢጌን እንዲሁም የተለያዩ አካላት በስነ ስርአቱ ታድመዋል ።
    በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ በመገኝት ንግግር ያደረጉት የቀበሌው ኮሙኒኬሽን እና የህብረተሰብ ተሣትፎ ልማት ማስተባበሪያ ሀላፊ አቶ #አብዱልአዚዝ አህመድ እንደተናገሩት የዚህ አነስተኛ ድልድይ ግንባታ የአካባቢው ነዋሪዎች በዝናብ ወቅትም ይሁን በሌላ ጊዜ የውሀ ፈሳሽ መወረጃ እና ተሸከርካሪዋች የማያሳልፈ በመሆኑ ለከፈተኛ ችግር በመጋለጣቸው ዘወትር የሚያነሱትን ጥያቄ መሆኑን አስታወሰው ለዚህም ሲባል በ2013 በጀት አመት ቀዳሚ በህብረተሰብ ተሣትፎ ልማት በቀበሌው ሊሰሩ ከታቀዱ የልማት ስራዎቸ ውስጥ በማካተት በአሁን ሰአት የድልድዩ በ2013 በጀት አመት ቅድሚያ በመስጠት በታቀደለት ጊዜ አጠናቀን የነዋሪውን ጥየቄ መመለስ እንደተቻለ እና ፕሮጀክቶችን መጀመር ብቻ ሳይሆን ማጠናቀቅ እንደሚገባን የተገነዘብንበት ነው ተብለዋል ።
    በሌላ በኩል የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላያ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የቀበሌው 09 ዋና ስ/አስፈፃሚ #አቶ ሀሰን ኢጌ ይህ ፕሮጀክት ለበርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው በመጥቀስ በቅርብ ጊዜ የቀሩት ፕሮጀክቶች እንደሚመረቁና በአዲስ በጀት አመትም 3 ፕሮጀክቶችን ለመስራት አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል ።
    #የተመረቀው ድላድዩ 7.25 ሜትር ርዝማኔ እና 6.75 ስፋት እንዳለው ለማወቅ ተችሏል፡፡
    የመረጃ ምንጭ፦የቀበሌ 09 ኮሙኒኬሽን ማስተባበሪያ