በ 1902 ዓ.ም ባቡር ከጅቡቲ ተነስቶ ወደ ድሬዳዋ መምጣቱን ተከትሎ በወቅቱ በርካታ የውጪ ሀገር ቱሪስቶች በባቡሩ ለመጓዝ ብሎም ባቡሩን ለመመልከት ወደ ድሬዳዋ ይመጡ ነበር ። ይህም በወቅቱ ለከተማዋ የቱሪዝም እድገት አይነተኛ አስተዋፆ እንደነበረው ይገለፃል ። ለዚህም ነው ድሬዳዋ ሲነሳ ባቡር እንዲሁም ባቡር ሲነሳ የድሬዳዋ ስም በጉልህ የሚነሳው ።
የአለም አቀፍ የቱሪዝም ቀን በሀገራችን ለ34 ተኛ እንዲሁም በአለም አቀፍ ደግሞ ለ42 ተኛ ጊዜ በመከበር ላይ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በታሪካዊው ባቡር የመጓዝ የጉብኝት መርሀ-ግብር በዛሬው እለት ተካሂዷል ። ይኸውም ጉብኝት መነሻውን ድሬዳዋ ምድር ባቡር አድርጎ ሽንሌ ደርሶ መልስ ያደረገ ሲሆን በጉብኝቱ መርሀ-ግብር ላይም የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች ፣ የወጣት የኪነ-ጥበብ ባለሞያች ፣ ጋዜጠኞች ፣ ተጋባዥ እንግዶችና ፣ ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል ።
በተለይም በታሪካዊው ባቡር ላይ የጉብኝቱ አንድ አካል በመሆናቸው መደሰታቸውን የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ተናግረዋል ።


