አሸባሪው የህወሀት ቡድን ሀገራችን ኢትዮጲያ ላይ እያደረሰ ያለውን ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት ብሎም የውሸት ፕሮፖጋንዳ የአሜሪካ መንግስትና መላው አለም አቀፍ ማህበረሰብ የሽብርተኛውን ቡድን ሴራ ይረዱት ዘንድ መላውን የአስተዳደሩን ነዋሪዎች በማስተባበር ” የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት ” በሚል መሪ ቃል ስለ አሸባሪው የህወሀት ሴራ ደብዳቤ ላይ በመፈረምና በፖስታ በማድረግ በዛሬው እለት የሚገኙ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ፊርማቸውን አኑረዋል
አሸባሪው የህወሀት ቡድን ሀገራችን ኢትዮጲያን ለማፈራረስ እያደረገ ያለውን ሴራ የአሜሪካ መንግስት ብሎም ምእራባዊያን እውነታውን መረዳት እንደሚገባቸው ተናግረው አሸባሪውን የህወሀት ቡድን መላው የሀገራችን ነዋሪዎች በጋራ በመሆን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመደምሰስ የሀገራችንን ብልፅግና ማስቀጠል እንደሚገባም በፊርማ ማኖር ስነስረዓቱ ላይ የተሳተፉ አመራሮች ገልፀዋል፡፡


