ነጩ ፖስታ ለነጩ ቤተ-መንግስት መርሀ-ግብር በድሬዳዋ አስተዳደር በይፋ ተጀምሯል ።

    አሸባሪው የህወሀት ቡድን ሀገራችን ኢትዮጲያ ላይ እያደረሰ ያለውን ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት ብሎም የውሸት ፕሮፖጋንዳ የአሜሪካ መንግስትና መላው አለም አቀፍ ማህበረሰብ የሽብርተኛውን ቡድን ሴራ ይረዱት ዘንድ መላውን የአስተዳደሩን ነዋሪዎች በማስተባበር ” የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት ” በሚል መሪ ቃል ስለ አሸባሪው የህወሀት ሴራ ደብዳቤ ላይ በመፈረምና በፖስታ በማድረግ በዛሬው እለት ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች በተገኙበት በይፋ አስጀምረውታል ።
    በዚሁ መርሀ-ግብር ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የሆኑት አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ በተለይም አሸባሪው የህወሀት ቡድን ሀገራችን ኢትዮጲያን ለማፈራረስ እያደረገ ያለውን ሴራ የአሜሪካ መንግስት ብሎም ምእራባዊያን እውነታውን መረዳት እንደሚገባቸው ተናግረው አሸባሪውን የህወሀት ቡድን መላው የሀገራችን ነዋሪዎች በጋራ በመሆን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመደምሰስ የሀገራችንን ብልፅግና ማስቀጠል እንደሚገባም አቶ አህመድ በእለቱ ተናግረዋል ።
    በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል አሸባሪው የህወሀት ቡድን እያካሄደው ያለውን ሀገርን የማተራመስ ሴራ በማስመልከት የፓርቲው ፅህፈት ቤት ከወጣቶች ሊግ ጋር በጋራ በመሆን ይህንን የአሸባሪውን ሴራ ለመቀልበስ ይቻል ዘንድ ነጩን ፖስታ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት በሚል መሪ ቃል የንቅናቄ ስራ መጀመሩን የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ምክትል ሀላፊና የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ ኡስማን አህመድ ተናግረው የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪዎችና ወጣቶች በንቃት በመሳተፍ ደብዳቤውን ለነጩ ቤተ-መንግስት ማድረስ እንደሚገባም ተናግረዋል ።
    ነጩ ፖስታ ለነጩ ቤተ-መንግስት መርሀ-ግብር ላይ የወጣቱ ሚና ከፍተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መላው የአስተዳደሩ ወጣቶች የራሳቸውን ጉልህ አስተዋፆ መወጣት እንዳለባቸውም የድሬዳዋ ወጣቶች ሊግ ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ የሆነው ወጣት ፈልመታ መሀመድ ተናግሯል ።
    በቀጣይ ቀናትም መሰል የተለያዩ መርሀ-ግብሮች እንደሚኖሩም ታውቋል ።