በአስተዳደሩ በገጠርና በከተማ ለሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤት ችግርተኛ ተማሪዎችድጋፍ ማድረጋቸውን የገለፁት የምስራቅ ሪጅን ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ ጣሰው ሽመልስ በትምህርት ላይ የሚደረግ ድጋፍ ለነገ በውቀት ሀገሩን ተረካቢ ዜጋ እንዲኖር ትልቅ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል፡፡
የአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት ኢትዮ ቴሌኮም ቀደም ባሉት ጊዜያት ለተቋማችን መምህራኖች እና ለተማሪዎች የተለያዩ ድጋፎች ሲያደርግ የቆየ ተቋም በመሆኑ አሁንም ተማሪዎች በደብተር ማጣት ከትምህርት ገበታቸው እንዳያቋርጡ ድጋፍ በማድረጉ በአስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎችም እንዲህ አይነት ድጋፎች ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ መግዛት የማይችሉ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ በማስቻሉ ትልቅ እገዛ በተለያዩ ተቋማት እየተደረገላቸው መሆኑን ገልፀው አመስግነዋል፡፡


