በፍጥነት እየተሰራጨ የሚገኝውን የኮቪድ 19 ዴልታ ዝርያ ለመግታት የሁሉንም አካላት እርብርብ እንደሚጠይቅ ተገለፀ።

    በዴልታ ዝርያ ምክንያት የተከሰተውን ሶስተኛው የኮቪድ 19 ማዕበል የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎችን ለማጠናከርና ባለድርሻ አካላትን ቅንጅታዊ አሰራር ለማጠናከር የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
    በመድረኩ የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ለምለም በዛብህ በድሬዳዋ አስተዳደር ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኮቪድ 19 ስርጭት አሳሳቢ በሆነ መልኩ እየተሰራጨ መሆኑን ገልጸው በየቀኑ በአስተዳደሩ ከሚመረመሩት ውስጥ 20 በመቶ ቫይረሱ እየተገኘባቸው እንደሆነና ባለፉት ሁለት ሳምንታት የአምስት ሠዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል።
    የቫይረሱ ሦስተኛው የስርጭት ማዕበል የተከሰተና የቫይረሱ ባህሪም ተለዋዋጭ በመሆኑ፣ በቫይረሱ የሚያዙና የሚሞቱ ሠዎች ቁጥር እየጨመረ ስለሚገኝም የስርጭት መጠኑን ለመግታት የተቀናጀ አሰራርን መተግበር እንደሚያስፈልግ ነው ሃላፊዋ የገለፁት።
    በዚህም የጥንቃቄ እርምጃዎችን መተግበርና የመከላከያ ክትባትን መከተብ አማራጭ የለውም ብለዋል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በበሽታው የሚያዙና የሚሞቱ ሠዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን÷ ለአብነት ያህል ከአዲሱ ዓመት በኃላ ደግሞ 285 ሰዎች ሲያዙ አምስቱ ደግሞ ህይወታቸውን ማጣታቸው ቢሮ ሃላፊዋ ገአስረድተዋል።
    በድሬደዋ ፖሊስኮምሽን የአስተዳ ልማት ዘርፍ ምክትል ኮምሽነር ውቢት ፍቃዱ የኮቪድ 19 ስረጭት ለመከላከል የወጡ አዋጆችን በጥብቅ ለማስፈጸም እንደሚራ ገልፀው የበለጠግን ህብረተሰቡ የህግ አካላትን ሳይጠብቅ አዋጁ የሚያዘውን በአግባቡ በመተግበር እራሱን ከበሽታው መጠበቅ አለበት ብለዋል።
    በመድረኩ የተሳተፉ የሃይማኖት አባቶች ኮሮና በዜጎች ላ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ለመከላከል የሃይማኖት ተቋማት ምእመናንን ማስተማር እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡ማንኛውም ሃይማኖታዊ ስነስረአት ስናካሂድ ኮሮናን ታሳቢ ባደረገ መንገድ ሊሆን ይገባል ሲሉ ለምእመናን ጥሪ አቅርበዋል