ተቋሙ እቅዱን ለማሳካት በከተማ 9ኙ ቀበሌዋች ከሚኖሩ ባለይዞታዋች ጋር ይዞታን ማረጋገጥና መመዝገብ ያለውን ጠቀሚታ የሚያስጨብጥ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሠጠ ነው።
ቀደም ባሉት ቀናት ለ4 ቀበሌዋች ግንዛቤ መፈጠሩን የገለፁት የመሬት ልማት እና ማኔጅመንት ቢሮ የከተማ መሬት ይዞታና ምዝገባ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሙና መሀመድ በቀጣይ ቀናት የቀሩ ቀበሌዋችን በማዳረስ በ2014 በጀት አመት ኤጀንሲው በእቅዱ የይዛቸውን 9600 ይዞታ ማረጋገጥ ስራውን ለማሳካትና ቀደም ባሉ አመታት የነበሩ ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ለባለ ይዞታዋች ግንዛቤ መፈጠሩ ስራውን የተቀላጠፈ ያደርገዋል ብለዋል።
ወ/ሮ ሙና አክለውም የከተማ መሬት ይዞታና ምዝገባ ኤጀንሲ እንደ ሀገር ሲቋቋም ከመሬት ጋር ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ታቅዶ በመሆኑ ስራው እታች ድረስ ወርዶ በመስራት እቅዱ ግቡን እንዲመታ የማህበረሰቡ እገዛ ወሳኝ ነው ብለዋል።
ወ/ሮ ሙና ከዚህም ጋር አያይዘው የቀበሌና የመንግስት ቤቶች የይዞታ ማረጋገጥ ስራ ውስጥ እንደሚካተቱ ጠቁመዋል።
በመድረኩ የተሳተፉ ተሳታፌዋች በሰጡት አሰሰተያየት እንደዚህ አይነት መድረኮች ቀደም ሲል ግንዛቤ አለመፈጠሩ በአመለካከታቸው ላይ ክፍተት መፍጠሩን በመጠቆም በቀጣይ እንዲህ አይነት መድረኮች ሊኖሩ ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ መጠናቀቃያ ከተቋሙ ጋር አብሮ ሊሰሩ
የሚችሉ አካባቢውን በደንብ የሚያውቁ የቅሬታና የታዛቢ ኮሚቴ ከተሳታፌዋች ተመርጧል።


