መልዕክተ ድሬ 741

    የኢትዮጵያን እውነት ለዓለም ለማሳወቅ ሁሉም ዜጋ የሀገሩ አምባሳደር
    በመሆን ሊሠራ ይገባል ተባለ

    በየደረጃው የሚገኙ የድሬዳዋ አስተዳደር አመራሮች የተሳተፉበትና አሸባሪው የህወሀት ቡድን እያደረገ ያለውን ኢትዮጲያን የማፈራረስ
    ሴራ ለአለመአቀፍ ማህበረሰብ የማሳወቅ አላማ ያለው <<ነጩ ፖስታ ለነጩ ቤተ-መንግስት>> መርሀ-ግብር በይፋ ተጀመረ።በመርሀ-ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር
    ከንቲባ የሆኑት አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ በተለይም አሸባሪው የህወሐት ቡድን ኢትዮጵያን
    የማፈራረስ ግልፅ አላማ አንግቦ ጦርነት ማወጁን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት የህግ የበላይነትን
    የማስከበር እርምጃ እወሰደ ባለበት በዚህ ጊዜ የሽብር ቡድኑ በተለያይ ማህበራዊ ሚዲያዎች
    የተሳሳቱ መረጃዎችን ለአለም በማሰራጨት ይገኛል ብለዋል። የሽብር ቡድኑ በሚያሰራጫቸዉ ሀሰተኛ
    መረጃዎችም አሜሪካን ጨምሮ ሌሎች ምዕራባውያንን በማሳሳት እና የቡድኑን ሀሰት እንደ
    እውነት እንዲቀበሉና በማሳመን በሀገር ላይ እያደረሰ ያለውን ጥፋት ከማውገዝ እና ተጠያቂ
    ከማድረግ ይልቅ አይተው እንዳላዩ በዝምታ ማለፍን እንዲመርጡ አድርጓቸዋልም ነው ያሉት
    ከንቲባው።…..ለበለጠ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ  መልዕክተ ድሬ 7 4 1 ሰኞ – መስከረም 17 /2014 ዓ.ም

    አዲሱን የኮቪድ 19 ዴልታ ዝርያ ስርጭቱንለመግታትም ሆነ ለመከላከል የሁሉንም አካላት ትኩረት እና ርብርብ ይጠይቃል ተባለ:-

    በዴልታ ዝርያ ምክንያት የተከሰተውን ሶስተኛው የኮቪድ 19 ማዕበል የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎችን ለማጠናከርና ባለድርሻ አካላትን ቅንጅታዊ አሠራር ለማጠናከር የሚያስችል የምክክር
    መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩ የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ለምለም በዛብህ
    በድሬዳዋ አስተዳደር ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኮቪድ 19 ስርጭት አሳሳቢ በሆነ መልኩ እየተሰራጨ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አክለውም በየቀኑ በአስተዳደሩ ከሚመረመሩት ውስጥ 20 በመቶ
    ቫይረሱ እየተገኘባቸው እንደሆነና ባለፉት ሁለት ሳምንታት የአምስት ሠዎች ህይወት ማለፉን
    አስታውቀዋል።ለበለጠ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ  መልዕክተ ድሬ 7 4 1 ሰኞ – መስከረም 17 /2014 ዓ.ም