መልዕክተ ድሬ 742

    በ3ኛ የሥራ ዘመን 49ኛ መደበኛ ጉባኤ የድሬዳዋ አስተዳደር
    ምሥረታ ተካሂዷል….ለበለጠ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ 

    የድሬዳዋ አስተዳደር ምስረታመስከረም 19/2014ዓም ተካሂዷል፡፡
    የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ተኛ የስራዘመን 1ኛ ዓመት 49ኛ ጉባኤው የተለያዩ ሹመቶችን ያፀደቀ ሲሆን በዚህም መሰረት የአስተዳደሩ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ በመሆንወ/ሮ ፈቲያ አደን እና የአስተዳደሩ ም/ቤት
    ም/አፈ-ጉባኤ በመሆን የተከበሩ ወ/ሮ ከሪማ አሊ ሮባን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡-መልዕክተ ድሬ 7 4 2 ሰኞ – መስከረም 24 /2014 ዓ.ም

    የብዙ ሙያዎች ባለቤትና የኢትዮጵያ ልጆች አባት

    በህዳር ወር 1957 ዓ.ም ላይ ነበር እስከዛሬም ድረስ መለያቸው የሆነውን “ጤና ይስጥልኝ
    ልጆች የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች” የሚለውን ሰላምታቸውን አስቀድመው በዘመኑ ብርቅዬ በነበረው
    ባለጥቁርና ነጭ ቀለሙ ቴሌቪዥን ለመጀመሪያ ጊዜ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ያሉት። እንዲህ እንደ ዛሬው
    ቴሌቪዥን በየሰው ቤት ሣይገባ የዘመኑ ልጆች የአበባ ተስፋዬን ተረትና ቀልዶች ለመስማት ቴሌቪዥን
    ላላቸው ጎረቤቶቻቸው የጉልበት ዋጋ ይከፍሉ ነበር፡፡ግቢ ማፅዳት፣ አትክልት መኮትኮት፣ ቆሻሻ መድፋት እና
    የመሳሰሉት ሥራዎች የወቅቱ ልጆች ለአባባ ተስፋዬ ተረትና ጨዋታ የሚከፍሏቸው ዋጋዎች ነበሩ፡፡-መልዕክተ ድሬ 7 4 2 ሰኞ – መስከረም 24 /2014 ዓ.ም