በስነ-ስረአቱ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ዳሬክተር ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ እንደተናገሩት ሀገራችን በዓለም አደባባይ ያላትን ገጽታ ለማበለሻት በተጠና መልኩ እየተንቀሳሰቀሱ ያሉ ሃይሎችን መረጃ ሃሰት መሆኑን ለማሳወቅ ሁላችንም የሀገር ገጽታን እና ያለውን እውነታ በመሰል የንቅናቄ መርሀግብሮች እና የማህበራዊ ገፆችን በመጠቀም ለውጭ አለማት ማስገንዘብ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
ሌላው ደግሞ አሉ ወ/ሮ ሰአዳ ከውጭ አለማት የኢኮኖሚ ተጽእኖ ለመላቀቅ ሁሉም በየተሰማራበት የሞያ መስክ ጠንክሮ በመስራት ሀገራችን በኢኮኖሚ ራስዋን ለመቻል እያደረገች ያለችውን እንቅስቃሴ ሊደግፍ ይገባል ብለዋል፡፡
እንደ ተቋምም ይህን ከዳር ለማድረስ የስራ ሰአትን ባግባቡ በመጠቀም እና ተገልጋይን በቅልጥፍና በማገልገል የድርሻችንን እንወጣለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በስነ-ስረአቱ ላይ ለተሳታፊዎቹ በወቅታዊ የሀገራዊ ጉዳይ ላይ ማብራርያ የሰጡት በተቋሙ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ጉልማ ታዬ እና ከአስተዳደሩ ወጣት ፌደሬሽን የተጋበዙት ወጣት ፈልመታ በበኩላቸው አሸባሪው የትህነግ ቡድን በመከላከያ ሰራዊታችን ላይ ጥቃት መፈፀሙ አልበቃ ብሎት በአፋር እና አማራ ክልል በንፁሃን ዜጎች ላይ
ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በመፈፀም የግፍ በደል እየፈፀመ ተበዳይ ለመምስል የሚያደርገውን የጥፈት ተግባር ተቀናጅተን በማክሸፍ እውነቱን ለአለም ልናሳውቅ ይገባል ብለዋል።
እውነታውን ወደ ጎን በመተው የተለያዩ የአለም ሚዲያዎቹ የሃገራችንን ስም ለማጉደፍ ብሎም ከእውነታው በተፃራሪ መልኩ መረጃዎችን እያሰራጩ በመሆኑ እውነታውን አለም እንዲያውቅ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ሲደረግ የነበረው ትግል በመቀላቀልም “የነጩ ፖስታ ወደ ነጩ ቤተመንግስት” በሚል የኢትዮጵያን ገጽታን ለማበላሸት የሚያደርግ እንቅስቃሴን ለማምከን የእለቱን መርሀግብር አካሂደናል ብለዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ ለዘመናት ነጻነቷን አስጠብቃ የኖረች ሀገር በኛ ዘመን አትደፈርም፣ እኛ ኢትዮጵያዊያን እያለን ኢትዮጵያ ሳትደፈር በዓለም ተከብራ ትኖራለች፣ የጥፋት ቡድን እኩይ ሴራ በልጆቿ የተባበረ ክንድ ይከሽፋል፣ በአሸባሪዉ ህዉሃት የወደሙ የትራንስፖርት መሠረተ ልማቶች በጋራ መልሰን እንገነባለን የሚሉ መልዕክቶች ተላልፈዋል።
ምንጭ የድሬደዋ መንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን


