ከገጠር የወጣቶች ሊግ ለተውጣጡ አባላትና አመራሮች በማህበራዊ ሚዲያ ምንነትና አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡

    ስልጠናው በማህበራዊ ሚዲያ ዙሪያ ግንዛቤ እንዳስጨበጣቸው በስልጠናው ተሳታፊ የሆኑ ወጣቶች ገልፀዋል፡፡
    በመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በመረጃ አካላትን ማብቃትና ማፍራት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀውን ስልጠና የሰጡት የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ሚካኤል እንዳለ ናቸው፡፡
    አቶ ሚካኤል በስልጠናው ስለ ማህበራዊ ሚዲያ ምንነት፣ጠቀሜታ እና ከማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የሚታዩ ክፍተቶችን በስልጠናው ዳሰዋል፡፡ ማህበራዊ ሚዲያን ባለማወቅ የተሳሳተ መረጃ የሚሰጡ እንዳሉ ሁሉ ሆንብለው ተልዕኮአቸውን ለማስፈፀም የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩ በመኖራቸው ወጣቶች መረጃዎችን በጥልቀት በማየትና በማስተዋል ማህበራዊ ሚዲያዎችን መጠቀም እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡
    በስልጠናው ተሳታፊ ከሆኑ ወጣቶች መካከል አንዳንድ ያነጋገርናቸው ወጣቶች እንደተናገሩት ስልጠናው ስለማህበራዊ ሚዲያ ምንነትና አጠቃቀም ዙሪያ ግንዛቤ እንዲጨብጡ አስችሏቸዋል፡፡ ከስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ ለሌሎች አቻዎቻቸውም እንደሚያጋሩ የገለፁት ሰልጣኞቹ ወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያን ሲጠቀሙ ለራሳቸውና ለሀገር በሚበጅ መልኩ መሆን እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡