የዴንጊ ትኩሳት በሽታ ወረርሽኝ በአስተዳደራችን መከሰቱን ተከትሎ ግብረ ሀይል ተቋቋመ

    የደንጊ ትኩሳት በሽታ ወረርሽኝ በየዓመቱ ዝናብን ተከትሎ እንደሚከሰት የሚታወቅ በመሆኑ በዚህ ዓመትም 87 ናሙና ወደ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተልኮ 4 ሰዎች በደንጊ ትኩሳት በሽታ መያዛቸውን የሚያረጋግጥ የምርመራ ውጤት መገኘቱን የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊወ/ሮ ለምለም በዛብህ ቀደም ብለው ለሚዲያ ባለሞያዎች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡
    የግብረሀይሉ ሰብሳቢ ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እና ም/ክ ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ፣የግብረሀይሉ ምክትል ሰብሳቢ የከተማ ስራአስኪያጅ ፅ/ቤት፣የግብረሀይሉ ፀሀፊ ጤናቢሮ ሲሆኑ በአባልነት፣ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ፣ ትምህርት ቢሮ፣ ግብርና ውሀ ማዕድን ኢነርጂ ቢሮ ፣ከንቲባ ፅ/ቤት ፣ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ፣ የኮንስትራክሽን ቤቶች ልማት አስተዳደር ፣ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን፣ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ፣ የሀይማኖት ተቋማት ጉባዔ፣ ቀይ መስቀል፣ እንዲሁም የግል ጤና ተቋማት አስተባባሪ ናቸው፡፡
    አገር የገጠማትን ችግር እየፈታን የበሽታ ምንጭ የሆነውን የተከማቸ ቁሻሻ ውሀን ከአስተዳደራችን ማጥፋ ይገባል ተብሏል፡፡
    ቀበሌዎች፣ሲቪክማህበራት፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ቆሻሻን እና ዲሽ ውስጥ የማይወርድ ውሀን በማስወገድና በቆሻሻ ሳቢያ የሚከሰትን የጤናና ማህበራዊ ችግሮች መከላከል እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
    ለቁሻሻ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ቆሻሻን ለማስወገድ መስራቱ ድሬዳዋን ፅዱና ውብ የመኖሪያ ስፍራ የማድረጉን ግብ ለማሳካት ያግዛል ያሉት ደግሞ ከትምህርት ቢሮ የመጡት አቶ ታመነ ወልደማሪያ ምናቸው፡፡