በድሬዳዋ አስተዳደር ዴልታ በመባል የሚታወቀውና በዓለማችን ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለው የኮቪድ ዝርያ ፣ እንዲሁም ደንጊ ፣ ቺክንጉኒያ እና ወባ አሳሳቢ በሚባል ደረጃ ተከስቷል ፡፡ ከዚህ ተደራራቢ ችግር ልንወጣ የምንችለው ማህበረሰባችን አሁን ያለንበትን ሁኔታ ተረድቶ እንደ አንድ ሆኖ የሚከተሉትን እርምጃዎች ሲወስድ ብቻ ነው ፡፡
እነሱም ፡-
1ኛ. ከቤታችን ውጪ ስንንቀሳቀስ የፊት ማስክ መልበስ ፣ አካላዊ እርቀታንን መጠበቅና እጆቻችንን ቶሎ ቶሎ መታጠብ ፣
2ኛ. ዘወትር አካባቢያችንን ማጽዳት፣ ንፅህናዉን በሚገባ መጠበቅና ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን ማፋሰስ ፣
3ኛ. ከትንኝ ንድፊያ የሚመጡ በሽታዎችን ለመከላከል በጸረ ትንኝ መድሃኒት የተነከሩ አጎበሮችን በመጠቀም ልንከላከል ይገባል ፡፡
በጋራ ጤናችንን እንጠብቅ!!
በጋራ የማናልፈውና የማንወጣው ችግር የለም !!!
የድሬዳዋ አስተዳደር!!!


