በድሬዳዋ የተከሰተውን የችኩንጉኒያ፣ የወባና የደንጊን ትኩሳት በሽታ ለመከላከል የፅዳት ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሄደ።

    በዛሬው እለት ንጋት 12:00 ጀምሮ በድሬዳዋ አስተዳደር የችኩንጉኒያ፣ የወባና ደንጊን በሽታ ለመከላከል የፅዳት ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጆሀርና አመራሮች እንዲሁም የድሬደዋ ነዋሪዋች በተገኙበት ተካሄዷል።
    በመረሀ ግብሩ የአስተዳደሩ ከንትባ አቶ ከድር ጆሀር ባስተላለፉት መልዕክት ይህ የፅዳት መረሀ ግብር በየሳምንቱ አመራሩ ወቶ ከማህበረሰቡ ጋር በማፅዳት ለህብረተሰቡ ምሳሌ ሆኖ ድሬደዋ ቀድሞ መጠሪያዋ የነበረውን ስሟን የመመለስ ስራ ተጀምሮ የሚቋረጥ ሳይሆን ቀጣይነት ያለው ስራ ሆኖ ይቀጥላል ብለዋል።
    ከንቲባ ከድር ከዚህም ጋር አያይዘው የንግድ ድርጅቶች አካባቢያቸውን ማፅዳት ይኖርባቸዋል በማለት ይህ ሳይሆን ከቀረ ቀደም ብሉ የወጣውን መመሪያና ደንብ ተግባራዊ በማድረግ የማሸግና የንግድ ድርጅቱን ፍቃድ እስከ መረከብ ድረስ እንደሚሰራ ገልፀዋል።
    የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፉ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ ባስተላለፉት መልዕክትም ማህበረሰቡ በሽታ ሲከሰት ተጎጂ የሚሆኑት እራሳቸው በመሆናቸው አካባቢያቸውን እና ግቢያቸውን በማፅዳት ከመስከረም እስከ ጥቅምት ወር በአስተዳደሩ ሊከሰቱ የሚችሉትን የችኩንጉኒያ፣ የወባና የደንጊን በሽታ ሊከላከሉ ይገባል ብለዋል።