የኮቪድ አደገኛ ዝርያ የሆነው የዴልታ ቫይረስ፣ የችኩጉኒያ፣ የደንጊ ና የወባ በሽታ ስርጭት እየጨመረ በመምጣቱ የተነሳ ከፍተኛ የመከላከል ስራ መሰራት እንዳለበት በድሬዳዋ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ የሚመራ ግብረሃይል ገምግሞ አቅጣጫ አስቀምጧል::
በዚህም ሁሉም የአስተዳደሩ ነዋሪዎችና ሰራተኞች በየሳምንቱ የመኖሪያ አካባቢያችንን እና የመስራያ አካባቢያችንን በሚገባ ማፅዳት ይኖሮብናል::
በድሬዳዋ አዲሱ አስተዳደር ከተዋቀረበት ጊዜ ጀምሮ የአስተዳደሩ ከንቲባና ካቢኔአቸው የአስተዳደሩን ነዋሪዎች በማስተባበርና በማሳታፍ የከተማዋን ፅዳት በአዲስ ምዕራፍ ጀምሯል።
በዚህም መሰረት ነገ ቅዳሜ መስከረም 29/2014 ዓ/ም የመጀመሪያው ዘመቻ ከታይዋን እስከ ገረኒ ሆቴል የፅዳት ዘመቻ ስለሚካሄድ ሁሉም የአስተዳደሩ የመንግስት አመራሮች ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ በዋናው ታይዋን መግቢያ በር ላይ እንድንገናኝ በተጨማሪም ሁሉም ሰራተኞች የመስሪያ አካባቢውን በዘመቻ እንዲያፀዳ እናሳውቃለን።
የድሬዳዋ አስተዳደር!!


