በአገር አቀፍ ደረጃ በተጀመረው አረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በሃገር ውስጥ ብቻ ተገድቦ እንዳይቀርና ለጎረቤት አገራት ችግኝ ለማቅረብ ከተያዘው እቅድ አንዱ የሆነው ለጅቡቲ ሪፕብሊክ የተዘጋጀው 40 ሺህ ችግኝ ዛሬ ተልኳል።
በችግኝ ሽኝቱ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ሁኔታው ከጎረቤት አገር ጅቡቲ ጋር ከኢኮኖሚያዊ ትስስር ባለፈ ኢትዮጵያ ያላትን በጋራ የመልማት ፍላጎትን ያንፀባርቃል ብለዋል።
በድሬደዋ አስተዳደር የአካባቢ የደን እና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን የደን ልማት እና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬከወተር አቶ ማስረሻ ይመር ለጅቡቲ ሪፕብሊክ የቀረበው ችግኝ በዘመናዊ መንገድ በበቂ ሁኔታ ተዘጋጅቶ መሆኑን አስረድተዋል።


