የ14 የሰንደቅ ዓላማ ቀን “በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ ሉዓላዊነት ለሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ” በሚል መሪ ቃል በድሬደዋ ተከበረ።

    የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል 4:30 ሰዓት በድሬደዋ በከተማና በገጠር አራቱም ክላስተሮች በእኩል ሰአት ተከብሯል።
    የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከልን ስርአትን በጠበቀ መልኩ ተከብሯል።
    የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጆሀር በስነ ስርአቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደተናገሩት የኢትዮጵያን አዲስ ምእራፍ መንግስት በተመሠረተበት እንዲሁም በመደመር እሳቤ ተባብረን የተደቀኑብንን ፈተናዋች ለመሻገር በአንድነት በተሰለፍንበት ወቅት የሚከበር በመሆኑ ከወትሮ የተለየ ያደርገዋል ብለዋል።