በሀገራችን ላይ የተካሄደው 6 ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊና ፍትሀዊ በሆነ አግባብ መካሄዱ ይታወቃል ። ይኸው ሀገራዊ ምርጫ በድሬዳዋ አስተዳደር ሲካሄድ በአስተዳደሩ በከተማም ሆነ በገጠር የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በነቂስ በመውጣት ይበጀኛል ብሎም ያስተዳድረኛል ብለው ያመኑበትን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ አግባብ መርጠዋል ። ከዚሁ ጋር ተያይዞም ምርጫው በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ የ 02 ቀበሌ የምስጋናና የእውቅና ፕሮግራም አዘጋጅቷል ።
በዚሁም መርሀ-ግብር ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የሆኑት አቶ ከድር ጁሀር የቀበሌ 02 እንደ አስተዳደር ሰፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ እናቶች ፣ የፀጥታ አካላቶች ፣ ወጣቶች ሌት ተቀን ምርጫው ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ ይከናወን ዘንድ ላደረጉት አስተዋፆ ምስጋናቸውን አቅርበው የመረጣቸውንም ህዝብ ዝቅ ብለው ለማገልገልም ቃል ገብተዋል ።
በአስተዳደሩ እንዲሁም በ 02 ቀበሌ ካሉት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ውስጥ ብልፅግና ፓርቲን በተሻለ ሁኔታ መርጠው ለድል ስላበቁት የድሬዳዋ የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
ኢትዮጲያ ትመርጣለች ብለን ጀምረን ኢትዮጲያ መርጣለች ፣ አሸንፋለች ፣ መንግስቷንም መስርታለችና ለዚህ ቀን በመድረሳቸውም በእለቱ ለተገኙት ተሳታፊዎች ምስጋናቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ እስቂያስ ታፈሰ አቅርበዋል ።
ሀገራችን ኢትዮጲያ እንድትወድቅ በርካታ ስራ በተሰራበት ህዝቧ ከመንግስት ወጣቱ ከመንግስት ፣ ሴቶች ከመንግስት ፣ በጋራ በመቀናጀት ኢትዮጲያ ላሸነፈችበት የድል ቀን መብቃታቸውን የ 02 ቀበሌ ዋና ስራ-አስፈፃሚ አቶ ወንድማገኝ በሻህ ተናግረው ህዝባችን በነቂስ ወቶ በመምረጥና ምርጫው ሰላማዊና ነፃ እንዲሆን ማድረግ መቻሉንም አቶ ወንድማገኝ ተናግረዋል ።
በፕሮግራሙ ላይም ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ፣ የከተማው ነዋሪዎች ፣ ወጣቶች ፣ ሴቶች ፣ ባለሀብቶች ፣ ባለድርሻ አካላት ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን 6 ተኛው ሀገራዊ ምርጫም በሰላም እንዲካሄድ የላቀ አስተዋፆ ላበረከቱ ወጣቶች ፣ ሴቶች ፣ የፀጥታ አካላት ፣ የመንደርና የቀጠና አደረጃጀቶች ፣ የምርጫ የእውቅና ሰርተፍኬትና ዋንጫ ከእለቱ የክብር እንግዶች እጅ ተቀብለዋል ። የተፎካካሪ ፓርቲዎችና የምርጫ ቦርድ ስራ አስፈፃሚ አመራርና አካላትም ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳበረከቱም ተገልፃል ።


