የድሬደዋ አስተዳደር ካቢኔ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የተለያዩ
ውሳኔዎችን አስተላልፏል…
የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ በአዲስ መዋቀሩ ተከትሎ አዲስ አሰራሮችን ለመዘርጋትና
ለመተግበር አቅዶ ወደ ስራ የገባ ሲሆን ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ ይቻለው ዘንድ መስከረም
26 ቀን 2014ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ የተላለፉትን
ውሳኔዎች በተመለከተ የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ
እስቅያስ ታፈሰ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡ ሲሆን በዚህም መሰረት፡-1. በከተማችን ድሬዳዋ ለሚስተዋለው የትራፊክ መጨናነቅና ከዚህም ጋር የተለያዩ ወንጀሎች ምክኒያት እየሆኑ ያሉትን ከባድ ተሸከርካሪዎች
ከከተማ እንዲወጡና በከተማችን የተሳለጠ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር እንዲሁም ከአደጋና
ከወንጀል የፀዳች ከተማን እውን ለማድረግ ይረዳ ዘንድ የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት
የአስተዳደሩ ካቢኔ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን በተገኘ በጀት ተገንብቶ አገልግሎት
ላይ የሚውል የከባድ ተሸከርካሪ ማቆሚያ የግንባታ መሬት በጅቡቲ መግቢያ ሙዲ አነኖ በሚባል አካባቢ 12 ሄክታር መሬት እንዲሰጥ ወስኗል፡፡……መልዕክተ ድሬ ሰኞ – ጥቅምት 1 /2014 ዓ.ም 7 4 3
የፎረንሲክ ሳይንስ ምንድነው?
እ.ኤ.አ. በ1248 ቻይና ውስጥ በሩዝ ማሳ አካባቢ ይሰሩ ከነበሩ ሰራተኞች መካከል አንደኛው
በስለት ተወግቶ ተገደለ፡፡ የገዳዩን ማንነት ለማወቅ ሁሉም የማሳው ሰራተኞች ለስራ የተሰጣቸውን ማጭድ
እንዲያመጡ ተደርጎ በረድፍ ተደረደሩ፡፡ ከተደረደሩት መካከል አንደኛዋን ማጭድ ዝንቦች ወረሯት፡፡ በዚህን
ጊዜ ገዳዩ ወዲያውኑ ተያዘ፡፡ ዝንቦቹ ያረፉት ደም የነካው ማጭድ ላይ ነበርና፡፡…..ለበለጠ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ ….መልዕክተ ድሬ7 4 3 ሰኞ – ጥቅምት 1 /2014 ዓ.ም 7 4 3


