በድሬዳዋ አስተዳደር የከተማው ክፍል በምሽት የመንገድ መብራት ችግርን በአፋጣኝ ለመቅረፍ በከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር የተመራ የሚመለከታቸው ባለድርሻዎች የተካተቱበት ልዑክ መስከረም 28/2014 ዓም ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ እኩለ ሌሊት ጉብኝት አድረጎ ነብር። ከጉብኝቱ በሗላም ውይይት ተደርጓል።በውይይቱም በመስክ ጉብኝቱ የታዩ ችግሮችን ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት የረጅም እና የአጭር ጊዜ እቅዶች ተቀምጠዋል።በዚህም መሰረት:-
1 በአጭር ጊዜ ፈጥነው ወደ ስራ መግባት የሚችሉ መስመሮች ተጠግነው ስራቸው እንዲጠናቀቅ።
2 ግዢና ተጨማሪ ግብአቶች የሚፈልጉ ስራዎች በካቢኔ ውሳኔ እነዲያገኙ በአፋጣኝ እንዲቀርቡ።
3 በዘላቂነት መፍትሄ ለመስጠት ተጨባጭ የሆነ ዝርዝር እቅድ ከሚመለከትው አካል /ከተማ ስራ አስኪሃጅ/ ማቅረብ እንዳለበት።
4 የኤሌትሪክ መብራት መስመሮች ላይ የሚፈጸም ስርቆት እንዲሁም መሰረተ ልማቶችን የማውደም ተግባርን ከጸጥታ አካላት ጋር በጋራ በመሆን መካላከል እንደሚገባ።ህብረተሰቡ ይህንን ተግባራ በንቃት ተከታትሎ አጥፊዎችን ማጋለጥ እንደሚገባው።
5 ለችግሩ መፍትሄ ለማበጀት በሚደረገው እንቅስቃሴ የሚያስፈልገውን በጀት ለመመደብ አስተዳደሩ ፍቃደኛ መሆኑን።
6 ህብረተሰቡ በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሱ ችግሮችን በመከላከል ብሎም መንግስት ከሚያከናውናቸው ልማቶች ጎን ለጎን በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን መጠገንና መገንባት እንደሚገባው የጋራ ተግባቦት ላይ ለመድረስ መሰራት እንዳለበት እቅድ ተቀምጧል።
በአጠቃላይ የከተማዋን በምሽት የመንገድ መብራት ችግር በአፋጣኝ ለመቅረፍ መከናወን ያለባቸው የአጭር እና የረጅም ጊዜ እቅዶች ተጠቃለው ለጥቅምት 14/ 2014 ዓም ለውሳኔ እንዲቀርቡ አቅጣጫ ተቀምጧል።


