“ያለፉትን ማክበር የዛሬዎቹን ማትጋት ነው!!” ይህን የተናገሩት በትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ዳሬክተር ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ ናቸው፡

    በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለረጅም አመታት በማገልገል በጡረታና በሞት ከተቋሙ የተለዩ ሰራተኞች እና ቤተሰቦቻቸውን ጉብኝት ተካሂዷል፡፡
    ወ/ሮ አሰጋሽ ከበደ በተቋሙ ከ1996 -2008 በሂሳብ ክፍል ባለሙያነት ሲያገለግሉ በድንገተኛህመም ተቋሙንከለቀቁ 6 አመት ሆኗቸዋል፡፡
    ታድያ ከምንም በላይ ሰውን ተርበዋልና ደንገት ከቤታቸው መቱትን ባልደረቦቻቸውን ሲያፊታቸው ፈክቶ እንባቸው በአይናቸው ሞልቶ ነበር የተቀበሉን፡፡
    በዋና ዳይሬክተሯ አማካኝነት የተዘጋጀውን ጥቂት ገንዘብና አስቤዛ ተረክበው በሁኔታው መደናገጣቸውን እና ፍፁም ደስታ እንደ ተሰማቸው ገልፀው ቀሪውን ለመናገር እንባ ቢንቃቸው አእጃቸውን በአይናቸው ጭነው አንገጣቸውን ደፉ፡፡
    ሌላዋ በቅርቡ በሞት የተለየችን ወሮ ትእግስት ቤት ሰሆን ያመራነው በዚያ የርሷን ታዳጊ ልጅ መክሊትን አገኘናት መክሊት ገና የእናትዋን ጉዋደኞች ስታይ ከኋላ እናቷን እምትፈልግ በሚመስል ስሜት ሁሉን በአይኗ ፈትሻ እጇን ለሰላምታ በመዘርጋት ከተቀበለችን በኋላ እንባ በአይኗ ሞልቶ መናገር ተስኗት በህፃን አንደበቷ ስላስታወሳችሁኝ አመሰግናለሁ በሚል ስሜት ሁላችንንም በአይኖቿ ቃኘችን፡፡
    እንባዋ ግን ፈፅሞ አላባራ ቢል የትምህርት ቦርሳዋን እና ጥቂት አስቤዛ እና ሳንቲም በዋና ዳይሬክተራችን ስም አበርክተን ተለያን፡፡
    በጉብኝቱ እርጅና ከተጫናቸው የቀድሞ ባልደረባችን አቶ አዳሙ በቅርብ እስከተለየን የቀድሞ የተቋሙ ኃላፊ አቶ መሀመድ ቤት አቅንተን አለን ከጎናችሁ ብለን የያዝናትን አበርክተን ተለያየን፡፡
    መሰል ተግባራት ሊጠናከሩ እንደሚገባ በተቋሙ የሰራተኞች የተሀድሶ ፕሮግራም ላይ መልእክት ያስተላለፉት ወ/ሮሰአዳ አዋሌ አንድ ተቋም ከሁሉ በላይ ለተሻለ አገልግሎት ሲነሳ አገልጋዩን በማመስገን ለሆን እንደሚገባ ገልፀው የቀደሙ የሰሩትን ማስታወስ የዛሩዎቹን ማበርታት ነው ብለዋል፡፡በቀጣም መሰል ፕሮግራሞች ተጠናክረውእንደሚቀትሉ በመግለፅ፡፡
    ትጉሀንን እናመሰግናለን ደንበኛ አማራሪ ሌባውን ከውስታችን በመንቀስ ለተሻለ ስራ እንተጋለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡
    በእለቱ የተለያዩ ሰራተኛውን አንቂ ፕሮግራሞቸም ተካሂደዋል፡፡
    ምንጭ፡-ፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ