መልዕክተ ድሬ 744

    የ14ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በአስተዳደሩ ተከበረ

    የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በሰዓት 4:30 በድሬደዋ በከተማና በገጠር አራቱም ክላስተሮች በእኩል ሰአት “በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ
    ሉዓላዊነት ለሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።

    ጥቅምት 1-2014ዓ.ም በአገር አቀፍ እና በአስተደዳሩ ለ14ኛ ጊዜ የኢፌዲሪ ሰንደቅ ዓላማ ቀን
    በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል፡፡ የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል ለ14ኛ ጊዜ “በአዲስ ምዕራፍ
    በተሟላ ሉዓላዊነት ለሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ” በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 1/2014ዓ.ም ተከብሯል፡፡
    ሰንደቅ ዓላማ የብሔራዊ አንድነት መገለጫ፤ የአንድ አገር ዜጎች አገራዊ ፍቅርና ብሔራዊ ስሜትን
    የሚገልፁበት፤ ታሪካዊ ትስስርና ስነ-ልቦናዊ አንድነት የሚንፀበረቁበት ነው፡፡ እንዲሁም የአገራዊ
    አንድነትና ህብረት አርማና ምልክት ነው፡፡በመሆኑም ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን በየዓመቱ
    ጥቅምት ወር በገባ በመጀመሪያው ሳምንት ሰኞ እንዲከበር በህግ የተደነገገ ነው……ለበለጠ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ መልዕክተ ድሬ 74 4ሰኞ – ጥቅምት 8 /2014 ዓ.ም

    የለውጥ ጉዞው፡-በእውነተኛ ፌዴራሊዝም ልዩነትን አቻችሎ ጠንካራ አገር የመገንባት ብሩህ ተስፋ

    የእውነተኛ ፌዴራሊዝም ሥርዓት መሰረታዊ ጉዳዩ በአንድ አገር የሚኖሩ ብሄሮችና ብሔረሰቦች ልዩነታቸውን
    አቻችለው በሁሉም መስክ የበለጸገች አገርን በመገንባት ሂደትውስጥ የሚገለጽ ነው። የራስ እና የጋራ አስተዳደርን እውን ማድረግ ደግሞ ሌላው ነጥብ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ
    ከለውጥ በፊት ሲተገበር የነበረው የፌዴራል ስርዓት የሁላችንም የምትሆን አገር ከመገንባት አኳያ ያልተመቸ፤ ይልቁንም ከአንድነት ይልቅ ልዩነት የጎላበትና የተሰበከበት ነበር…..ለበለጠ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ መልዕክተ ድሬ74 4ሰኞ – ጥቅምት 8 /2014 ዓ.ም

    በትክክለኛ ምክኒያት ላይ የተመሠረተ አመለካከት በመያዝ ለውጡን እናስቀጥል

    በምንኖርባት በዚህች ዓለም ለሚከሰቱ ክስተቶች በሙሉ የራሳቸው ምክኒያት አላቸው፡፡ ለዚህም ነው አንድ ክስተት ሲከሰት የሁሉም ሰው የመጀመሪያ ጥያቄው ለምን፣ ከዚያ ሲያልፍ
    ደግሞ እንዴት እያለ የሚቀጥለው፡፡ የዕለት ተዕለት ኑሯችን በክስተት የተሞላ ስለሆነ ለሚከሰቱ ክስተቶች ሁሉ በተጨባጭ ማስርጃዎችናመረጃዎች የተደገፈ ምክንያት ሊኖረው ስለሚችል ጠይቆና መርምሮ
    ማወቅ ብልህነትና የስልጣኔያችን አንዱ መገለጫ ሊሆን ይገባል…ለበለጠ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ መልዕክተ ድሬ74 4ሰኞ – ጥቅምት 8 /2014 ዓ.ም