አገራችን ኢትዮጵያ ከድህነትና ኋላቀርነት ተላቃ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ለማሰለፍና የአፍሪካ አገሮች የብልጽግናተምሳሌት ለማድረግ የሚያስችሉ አገር በቀል የኢኮኖሚ
ፓሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በመንደፍ የተቀናጀ የልማት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡ በአገራችን በተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ የልማት ተግባራትም ለተጀመረው
የብልጽግና ጉዞ መሰረት የሚጥሉ ውጤቶች በመመዝገብ ላይ ናቸው፡፡በተለይም ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ መንግሥት፣ልማታዊ ባለሃብቱና ህዝቡ ባደረጉት የጋራ እንቀስቃሴ አበራታችና
ተስፋ ሰጭ ውጤቶች የተመዘገቡትም በተለያዩ የልማት ዘርፎች (ሴክተሮች) ነው፡፡ባለፉት ሶስትና በላይ ዓመታት በሃገራችን እየተመዘገቡ ለሚገኙ የልማት ውጤቶችና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት
የግብርናው ዘርፍ የሚያበረከተው ጉልህ ድርሻ እንደተጠበቀ ሆኖ ሌሎች ዘርፎችም አስተዋጽኦ ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ በዚህም ረገድ በዋነኛነት የሚጠቀሰው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ነው፡፡
የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ለሃገራችንም ሆነ ለአስተዳደራችን የኢኮኖሚ ዕድገት እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው የሚያሰኘውም ለዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠራና ለከተሞች
ልማት፣ወዘተ መጎልበትና ለብልጽግና ጉዟችን መፋጣን ያለው የልማት ድርሻ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ነው፡፡ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ለአገራችን ኢኮኖሚ ዕድገትና ለድህነት
ቅነሳ ያለው ድርሻ እየጨመረ የመጣውም ከ2007 ዓ/ም ጀምሮ ሲሆን ባለፉት ሶስት ዓመታትም ለአገራችን ዓመታዊ የምርት ዕድገት ያበረከተው አስተዋጽኦ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ምክንያቱም በቀደምት
ዓመታት ከነበረበት ዝቅተኛ የዕድገት ደረጃ በ2007 ዓ/ም የበጀት ዓመት ከጠቅላላው ሃገር ውስጥ ዓመታዊ ምርት ዕድገት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ድርሻ 8.5% (በመቶ) እንደነበረ
መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በአሁኑ ወቅትም 12.5% (በመቶ) የሚሆነውን ድርሻ እንደያዘ የሚያመለክቱ ማስረጃዎች አሉ፡፡……ለበለጠ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ የድሬዳዋ አስተዳደር የኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ መልዕክት ጥቅምት 2014
የድሬዳዋ አስተዳደር የኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ መልዕክት


