የድሬዳዋ አስተዳደር የኮንስትራክሽን እና የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ
1. መግቢያ
የአገርን ዕደገትና ብልጽግና የሚያረጋግጡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ውጤቶችን ለማስመዝገብ ከሚያስችሉ፣ መሰረት ከሚሆኑና
የገቢ ምንጮችን ለመፍጠርም ሆነ ለማስፋት የሚረዱ ናቸው ተብለው ቅድሚያ ከሚሰጣቸው የልማት ዘርፎች መካከል በግንባር ቀደም
የሚጠቀሰው የመሰረተ ልማት አቅርቦት ወይም የግንባታው የልማት ዘርፍ ነው፡፡ ይህም ዕውነታ በሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን በእንስሳትም
እንደሚታወቅ የሚጠቁም አባባል አለ፡፡ምክንያቱም “መጀመሪያ መቀመጫዬን አለች ዝንጀሮ” የሚባለው ለማንኛውም የሥራ እንቅስቃሴ
ምቹ ሁኔታ ለመፍጠርም ሆነ ውጤታማነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ግብዓቶች በሚታሰቡበት ወቅት ልክ ዝንጀሮዋ እንዳለችው ቅድሚያ
የሚሰጠው የሚኖርበት፣ አገልግሎት የሚሰጥበትና ምርት የሚመረትበት ቦታ ወይም ግንባታ (ቤት) ነው፡፡ ይህም የግንባታ ግብዓት ጥያቄ
ከመኖሪያ ቤት ጀምሮ አገልግሎት ለመስጠትና ለማምረቻነት ታስበው የሚገነቡ መንገዶችን፣ ሆቴሎችንና የመዝናኛ ቦታዎችን፣
የፋብሪካዎችንና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የሚያስፈልጉ ማምረቻዎችን፣ የምርት ውጤቶችን ለማስቀመጥ የሚያገለግሉ መጋዘኖችን ፣ ወዘተ
ግንባታዎችን የሚያጠቃልል ነው፡፡ የእነዚህም የአገልግሎት መስጫ ተቋማትና የማምረቻ ድርጅቶች የግንባታ ሂደት የሚመራውም ሆነ
ለውጤታማነታቸው መሰረት የሚጥል የሙያና የቴክኒክ ድጋፍ፣ የክትትልና የቁጥጥር አገልግሎት የመስጠት፣ የህብረተሰቡን ተሳትፎ
የማረጋገጥ፣ የድሬዳዋ አስተዳደርን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የመምራት ስልጣንና ሃላፊነት ያለው የኮንስትራክሽንና የቤቶች ልማትና
አስተዳደር ቢሮ ነው፡፡ ይህም በአዋጅ የተሰጠው ስልጣንና ሃላፊነት የሚያመለክተው ተቋሙ ማንኛውንም የግልና የመንግስት ግንባታዎች
የመከታተልና የመቆጣጠር፣ የጥራት ደረጃቸውንና ደህንነታቸውን ጠብቀው እንዲገነቡ የማድረግና በግንባታው ሥራ ላይ የመወሰን ስልጣን
ያለው መሆኑን ነው፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር የኮንስትራክሽን እና የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአዋጅ የተሰጠው ስልጣንና ሃላፊነት የሚያመለክተውም ቢሮው
በሥሩ በተደራጁ ተጠሪ ተቋማትና የሥራ ሂደቶች አማካኝነት የሙያና የቴክኒክ ወይም የዲዛይን ዝግጅትና ግምገማ ፣ የግንባታ ሥራዎች
የውልና የኮንትራት አስተዳደር ድጋፍ የመስጠት፣ በግንባታ ቦታዎች በአካል በመገኘት የግንባታዎችን ሥራ የግንባታ ሂደትና አፈፃፀም
የመከታተልና የመቆጣጠር ስልጣን የተሰጠውም የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ለአገር ልማትና ብልጽግና የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ
ስለሆነ ብቻ አይደለም፡፡ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የልማት ፋይዳ ከፍተኛ ቢሆንም የግንባታዎች ጥራትና ደህንነት ካልተጠበቀ
የሚደርሰው አደጋም አገርንና ማህበረሰብን የሚያከስር መሆኑ ስለሚታወቅ ነው፡፡ ዘርፉ ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል የሚፈጠርበትና ለአገር
ኢኮኖሚ ዕድገት መሰረት የሚጥል ገቢ የሚመነጭበት በመሆኑም የጥራት ደረጃቸውን የተጠበቁ፣ ደህንነታቸው የተረጋገጠ፣ ለአገልግሎት
አሰጣጥ ምቾት ያላቸውና የከተማውን ውበት የሚጨምሩ የግንባታ ውጤቶችን መገንባት ያስፈልጋል…...ለበለጠ መረጃ ስለ ቢሮው ራዕይ ፣ተልዕኮና ዕሴቶች፣. የቢሮው አጭር መግለጫ፣…ወዘተ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ…..የድሬዳዋ አስተዳደር የኮንስትራክሽን እና የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ መረጃ ጥቅምት 2014 ዓ/ም
የድሬዳዋ አስተዳደር የኮንስትራክሽን እና የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ


