ፕሮፌሽናል ብስክሌተኛ በመሆን የሀገሩን ስም የማስጠራት ራእይ እንዳለው የአለም ሻምፒዮና ተሳታፊ የሆነው ኪያ ጀማል ተናግሯል ።

    ፕሮፌሽናል ብስክሌተኛ በመሆን የሀገሩን ስም የማስጠራት ራእይ እንዳለው የአለም ሻምፒዮና ተሳታፊ የሆነው ኪያ ጀማል ተናግሯል ።
    የብስክሌት ስፖርት በሀገራችን ኢትዮጲያ በስፋት የሚዘወተር ስፖርት ሲሆን ይህም ስፖርት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሀገራችን ኢትዮጲያ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ላይ ውድድሮች እየተካሄዱ ከሀገራችን አልፎ በአህጉራችን አፍሪካ ብሎም በአለም አደባባይ በብስክሌት ስፖርት የሀገራችን ኢትዮጲያን ስም በጉልህ የሚያስጠሩ ስፖርተኞችን ማፍራት ተችሏል ።
    ከነዚህም ስፖርተኞች ውስጥ ኪያ ጀማል አንዱ ነው ። ኪያ የአንጋፋውና በሞስኮ ኦሎምፒክ ላይ ሀገሩን ወክሎ መሳተፍ የቻለው ብስክሌተኛ ጀማል ሮጎራ ልጅ ነው ። ኪያ ብስክሌትን ለመጀመር ምክንያቱ ወላጅ አባቱ እንደሆነና በክለብ ደረጃ አሁን ላይ የድሬዳዋ ፖሊስ ስፖርት ክለብ ተወዳዳሪ ሲሆን በ 2013 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የብስክሌት ሻምፒዮና አዳማ ላይ ሲካሄድ በዛ ውድድር ላይ ባስመዘገበው ጥሩ ውጤት መሰረት ግብፅ ላይ ለተካሄደው የአፍሪካ ብስክሌት ሻምፒዮና ላይ መሳተፍ ችሏል ። በግብፅ በተካሄደው የአፍሪካ ሻምፒዮና ውድድር ላይም ጥሩ የሚባል ውጤት ማስመዘገቡን ኪያ ጀማል ተናግሯል ።
    ግብፅ ላይ ባስመዘገው ውጤት መሰረትም ቤልጂየም ላይ ለተደረገውና ለ 100 ኛ ጊዜ በተካሄደው የአለም ሻምፒዮና ላይ ሀገሩ ኢትዮጲያን ለመወከል ችሏል ። በዚህ ውድድር ላይም ከመሳተፍ ባለፈ ከ 19 አመት በታች አፍሪካን ወክለው ከተሳተፍ ሌሎች ሀገሮች የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል ።
    ኪያ ቤልጂየም ላይ ሄዶ ለመወዳደር እገዛ ያደረገለትን የኢትዮጲያ ብስክሌት ፌዴሬሽንን አመስግኖ በቀጣይም ፕሮፌሽናል ብስክሌት ተወዳዳሪ የመሆን ህልም እንዳለውም ኪያ ጀማል ተናግሯል ።
    ኪያ በተለያዩ ጊዜያቶች ትሬሊንግ በሚሰራበት ሰአት እንዲሁም በውውድር ወቅት ከማበረታታት አንስቶ በስፖርቱ ውጤታማ ይሆን ዘንድ ዘርፈ-ቡዙ ድጋፎችን እንደምታደርግለት ወላጅ እናቱ የሆኑት ወ\ሮ ፍፁም ተናግረው ሌሎች ወላጆችም ልጆቻቸው በስፖርት ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ ድጋፍ ሊያደርጉላቸው እንደሚገባም ወ\ሮ ፍፁም ተናግረዋል ።