ኢትዮጵያ በከሀዲው ጁንታ እየተወጋች ነው ፡፡ በጁንታው አዘውንት ፣ ሴቶች ፣ ህጻናት ፣ ወጠቶች ሁሉም ኢተዮጵያዊ ስለሆኑ ብቻ አሰቃቂ ሞት ተፈጽሞባቸዋል ፡፡
በሰሜን ኢትዮጵያ ያሉ ከተሞች አንበጣ የማሽላ ማሳን እንደሚያወድም ጁንታውም ትምህርት ቤቶችን ፣ የህክምና መዕከላትን ፣ የቴሌኮም መሰረተ ልማቶችን ፣ የኤሌክትሪክ መስመሮችን ፣ ባንኮችን እና የአገልግሎት ተቋማትን የቻለውን ሁሉ እየዘረፈ ያልቻለውን በእሳት እያቃጠለ ይገኛል ፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የጸጥታ ኃይል በዓለም አቀፍ የጦርነት ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ገድል የፈጸመና ሀገርን የታደገ ጠንካራ መከታችን ነው ፡፡ በዓለም አደባባይ ዜጎች እንኳንም ከኢትዮጵያ ተፈጠርን ብለው አንገታቸውን ቀና አድረገው እንዲሄዱ ያስቻለ ድንቅ ሰራዊት ነው ያለን ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር መከላከያ ኃይላችንና የጸጥታ ኃይሉ እየከፈሉ ላሉት መስዋትነትና ለሚፈጸሙት ታሪክ ታላቅ ክብር አለው ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደርና የድሬዳዋ ህዝብ በቀጣይ ለሚደረገው የህልውና ጦርነት ከሀገር መከላከያ ራዊት ጎን በመሰለፍ ጦርነቱ በአጭር ጊዜ ኢትዮጵያ አሸናፊ ሆና እንድትወጣ የምንሰስተው ሀብት ፣ የምናከመቸው ቁስ አይኖረንም ፡፡
በጦርነቱ ጉዳት ደርሶባቸው በተለያዩ መጠለያ ጣብያዎች የሚገኙ ወገኖቻችንን የማቋቋም ግዙፍ ስራ የድሬዳዋ አስተዳደርና ህዝብ ዋንኛ ቁልፍ ተግባር ነው ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር አመራር ለሀገር ህልውና የሀገራዊ የክተት ዘመቻ ጥሪን ተከትሎ ወቅቱ የሚጠይቀውን ማንኛውንም ሀገራዊ ኃላፊነት ህዝባችንን በማሰለፍ እና በማስተባበር አውደ ውጊያው ድረስ በመዝመት እስከ ህይወት መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን አረጋግጣለው፡፡
በድሬዳዋ አስተዳደር የምትገኙ ወጣቶች ፡- የነገ ተሰፋችሁን ለማጨለም ጁንታው በኢትዮጵያ ላይ የህልውና አደጋ ጋርዷል ፡፡ ወጣቱ ከአባቱና ከአያቱ የተረከባትን ሀገር እሱም በተራው ከነነጻነቷና የግዛት አንድነቷ ለቀጣዩ ትውልድ የማስረከብ ታላቅ ኃላፊነት በትከሻው ላይ ወድቋል ፡፡
በመሆኑም ከመንግስት የቀረበልህን የህልውና ዘመቻ የክተት ጥሪ በመቀበል የህይወት መስዋትነት ጭምር በመክፈል ሀገርን እንድትታደግ ጥሪ እናቀርባለን ፡፡
ቀሪው የድሬዳዋ ህዝብም ከሀገር መከላከያ ፣ ከፌደራል ፖሊስ ፣ ከድሬዳዋ ፖሊስና ልዩ ኃይል ጋር በመናበብ ጸጉረ ልውጦች ሲመጡ በማሳወቅ አካባቢህን ነቅተህ መጠበቅ ወቅቱ የሚጠይቀው የዜግነት ግዴታታህን እንድትወጣ ጥሪ አቀርባለሁ ፡፡
ኢትዮጵያ ታሸንፋለች !!! የብልጽግና ጉዟችን በጁንታው መሰሪ ተንኮልና ተላላኪነት አይደናቀፍም !!!


