የቅዳሜና እሁድ የአስቤዛ ገበያ በድሬደዋ ተጀመረ።

    የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በድሬዳዋ አስተዳደር በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች የቅዳሜና እሁድ ገበያ እንደሚጀመር የአስተዳደሩ የንግድ፤ኢንዱስትሪ እና ኢኒቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ።
    በነገው እለት የሚጀመረው የቅዳሜና እሁድ የገበያ አገልግሎት ከከዚራ ቤተ መንግስት ጀምሮ እስከ ብሔራዊ ሆቴል ዋና መንገድ ላይ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ዘይት፣ስኳር እና የፋብሪካ ውጤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚቀርብ ተቋሙ አስታውቋል።
    አላማው ሸማችና አምራችን በቀጥታ በማገናኘት የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በየሳምንቱ ቅዳሜና እሁድ ግብይቱ በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተቋሙ አስታውቋል።
    በሳምት ሁለቱን ቀን የከተማው ማህበረሰብ ቦታው በመገኘት በተመጣጣኝ ዋጋ ግብይት እንዲፈፅም የአስተዳደሩ የንግድ፤ኢንዱስትሪ እና ኢኒቨስትመንት ቢሮ ጥሪ አቅርቧል።
    ልብ ይበሉ !! <<ከከዚራ ቤተ መንግስት ጀምሮ እስከ ብሔራዊ ሆቴል ዋና መንገድ >> መሆኑን አፅዕኖት መስጠት እንወዳለን