ህዳር 8/2014 ዓ.ም በአስተዳደሩ የብልጽግና ፓርቲ አባላት የሆኑ የመንግስት ሠራተኞች በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ለውይይት የቀረበው ሰነድ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና የመንግስት ሰራተኛው ሚና ምን መሆን አለበት በሚሉ ርዕሶች ዙሪያ በዝርዝር ቀርቧል።
ሀገር ሰላም ሲሆን ሁሉም የመንግስት ተቋማት የተቋቋሙለትን አላማ ማሳካት ስለሚችሉ በየተቋማት ያሉ የፓርቲው አባል የሆኑ የመንግስት ሠራተኞች የሚጠበቅባቸው ድርሻ እንዲወጡ የድሬዳዋ የመንግስት ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ጠይቀዋል።
እንደ ድሬዳዋ የአሸባሪውን ጁንታ ሴራ በማጋለጥ ከጀግናው መከላከያ ሰራዊት ጎን በመሆን ሀገራዊ ሁኔታን በአግባቡ በመረዳት የተጋረጠብንን የህልውና ጉዳይ ለመቀልበስ እንዲያስችል ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆን የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከዲር ጁሀር ገልጸዋል።
የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር በማስቀጠልም ለመንግስት ሰራተኛው ባስቀመጡት የስራ አቅጣጫ የመንግስት ሰራተኛው ማህበረሰቡን በቅንነት በታማኝነት ማገልገል እንዲሁም የስራ ቦታቸውንና አካባቢያቸውን ፅዱና ማራኪ በማድረግ የመንግስት ስራ ሰዓትን ሙሉ ጊዜ በመስራት አርያ መሆን ይኖርባችዋል ብለዋል።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የአስተዳደሩ የመንግስት ሠራተኞች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ በተካሄደው የንቅናቄ መድረክ የአሸባሪውን ጁንታ ሴራን ለማጋለጥና እና ከጀግናው መከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናቸው በመግለጽ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።


