በሀገራችን የተጀመረው ኢትዮጵያን የማፍረስ የሚድያ ዘመቻ በግልፅ በመረዳት የድሬዳዋ አስተዳደር የማህበራዊ ሚድያ ሰራዊት እና አመራሮች ትክክለኛ መረጃዋችን በማውጣት ኢትዮጵያን በማዳን ዘመቻ የድርሻቸውን መወጣት የሚያስችል የኮሙዩኒኬሽንና የሚድያ የግንዛቤ ማዳበሪያ ስልጠና ተሰጠ።
በሀገራችን የተጀመረው ኢትዮጵያን የማፍረስ የሚድያ ዘመቻ በግልፅ በመረዳት አደጋውን ለመቀልበስ በዚህ ልክ የተደራጀ የሚዲያና የኮሙዪኒኬሽን ሠራዊት በማጠናከር ሀገራችን ን ለማዳን በምናስፈልጋት ሁሉ በ የድርሻችንን መወጣት ይገባናል ያሉት የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ለግንዛቤ ማዳበሪያ ስልጠና ተሳታፉዋች ባስተላለፉት መልዕክት በኢትዮጵያ ላይ የተዘረጋውን የሚድያ ዘመቻ ለመቀልበስ ለማህበረሰቡ ትክክለኛ መረጃዋችን በማውጣት ግንዛቤ እንዲያገኙ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል።
አቶ ኢብራሂም ከዚህም ጋር አያይዘው በህዝብ ተመርጦ ወደ ስልጣን የመጣውን መንግስት በማፍረስ ለነሱ ተላላኪ የሆነ መንግስት ለመመስረት በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተውን ዘመቻ ለመቀልበስ ትክክለኛ መረጃን በማውጣት ህዝቡን የማንቃት ስራ ከኛ ከልጆቿ ይጠበቃል ብለዋል።
የአስተዳዳሩ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ በበኩላቸው ባቀረቡት ሰነድ ማህበራዊ ሚዲያዎች በሀገር ማፍረስ ላይ ያላቸውን ተፅዕኖና ሊያስከትሏቸው የሚችሉትን ቀውስ የዳሰሰ ፅሁፍ አቅርበዋል።እንዲሁም የአስተዳደሩ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፉ አቶ ሚካኤል እንዳለ የማህበራዊ ሚዲያን የሚዳስስ ፅሁፍ አቅርበው በቀረቡት ሰነዶች ላይ ተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
በስልጠናው የተሳተፍ ወጣቶች በመድረኩ የተፈጠረላቸውን አቅም በመጠቀም ከምዕራባውያን ሀገራት የሚወጡ ሀሰተኛ መረጃዋችን እውነተኛ መረጃዋችን በማሰራጨት ሀገራቸውን የማዳን ስራ
ለመስራት በምንችላቸው ቋንቋዋች ሁሉ ትክክለኛ መረጃ በመስጠት ሀገርን ከመፍረስ ለማዳን ዘብ እንቆማለን ብለዋል።


