ለ16ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሔረሰብ በዓል አከባበር የተለያዩ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸው ተገለፀ ።
በድሬዳዋ የሚከበረው 16ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሔረሰብ በዓል አከባበር አስመልክቶ በክቡር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ የሚመራው የበዓሉ ዝግጅት ንዑሳን ኮሚቴዎች እስከ ዛሬ ድረስ የተሰሩ ስራዎች ገምግሟል።
በግምገማው እስካሁን የተከናወኑት ተግባራት የገመገሙ ሲሆን የአስተዳደሩ ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊና የምክር ቤቱ ፀኃፊ የተከበሩ አቶ ስንታየሁ ማሞ አጠቃላይ ስራዋች አስመልክቶ እንደተናገሩት ለ16ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሔረሰብ በዓል በአስተዳደሩ ስናከብር ሀገራችን ካጋጠማት ወቅታዊ ችግር ጋር ተያይዞ በአውደ ዕርይና በተለያዪ ጥናታዊ ሰነዶች በማቅረብ የተለያዪ ዝግጅቶች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።
ጽ/ቤት ኃላፊ ከዚህም ጋር አያይዘው በአሉ ያለምንም ፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ የአስተዳደሩ የበላይ አመራሮች ከአጎራባች ክልሉች ጋር በተቀናጀና በተናበበ መልኩ በመሆን ኮማንድ ፖስት ተዋቅሮ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ጽ/ቤት ኃላፊ አክለውም የአስተዳደሩ ማህበረሰብ የበአሉ ባለቤት በመሆኑ የድሬዳዋ ባህል የሆነውን ፍቅር በመስጠትና ወንድማማችነትን በማሳየት በዓሉን ሊታደሙ የሚመጡ እንግዶቻችንን ልናስተናግዳቸው ይገባል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ብሄር ብሔረሰብ በዓል አከባበር ኮሚቴዋች በቀሪ ቀናቶች የሚሰሩ ስራዎች ላይ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ስብሰባውን አጠናቋል።
<ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ለጋራ ብልፅግና>


