የተማሪዎች የአደንዛዥ እፅና የአደጋ ተጋላጭነት መቀነስ ላይ ትኩረት ያደረገ የውይይት መድረክ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል ።

    የተማሪዎች የአደንዛዥ እፅና የአደጋ ተጋላጭነት መቀነስ ላይ ትኩረት ያደረገ የውይይት መድረክ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል ።
    የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ቢሮ የሴቶች ማሳተፍ ማብቃትና ስራዓተ ፆታ ስርፀት ዳይሬክቶሬት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሴቶችና ወጣቶች ኤች.አይቪ ኤድስና ልዩ ፍላጎት ዳይሬክቶሬት ጋር በጋራ በመተባበር ተማሪዎች አዘውትረው በሚውሉበት ማህበረሰብ አካባቢ ተማሪዎች የአደንዛዥ እፅ ተጋላጭነት መቀነስ ላይ ትኩረት ያደረገ የውይይት መድረክ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል ፡፡
    በተለይም በከተማችን ድሬዳዋ ላይ የአደንዛዥ እፅ ተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን የድሬደዋ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ገልፀው ከአደንዛዥ እጽ ተጠቃሚዎች መካከልም የከፍተኛና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ቁጠር ቀላል የማይባል ድረሻ እንደያዘና የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲም ለችግሩ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ ከቢሮው ጋር የጀመረው እንቅስቃሴ ይሳካ ዘንድም ቢሮው የበኩሉን ሚና እንደሚወጣም ወ\ሮ ፈጡም በእለቱ ተናግረዋል ።
    ይህንን አሳሳቢ ችግር ለመቅረፍ ዩኒቨርሲቲው ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እንቅስቃሴ እያደረገ ቢሆንም ችግሩን ትርጉም ባለው መልኩ መቅረፍ እንዲቻል ግን አብዛኛው ተማሪዎች አዘውትረው በሚውሉበት ነዋሪ የሆነው የዩኒቨርሲቲው አካባቢ ማህበረሰብ ትልቁን ሚና ሊጫወት እንደሚገባም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ተወካይና የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንት የሆኑት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም ተናግረዋል