ዜና እረፍት

    ወ/ሮ ስንዱ ከበደ በድሬደዋ አስተዳደር ዕንባ ጠባቂ ተቋም የስራ ባልደረባ የነበሩ ለስራ ወደ አዳማ አቅንታ ከአዳማ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ ሳሉ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በ 18/03/2014 ህይወታቸው አልፉል ፡፡
    ወ/ሮ ስንዱ በድሬደዋ አስተዳደር በተለያዩ ተቋማት በሃላፊነት እና በከፍተኛ ባለሞያነት ያገለገሉ ናቸው።
    ወ/ሮ ስንዱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኬሚስትሪ ሳይንስ በዲግሪ
    ከሓረማያ ዩኒቨርሲቲ Master of Art Degree in Vocational Education Management ያገኙ ሲሆን በተለያየ ሙያ ፦
    – በደደር ከተማ አጠቃለይ ሁለተና ደረጃ ት/ቤት በመምህርነት
    – በድሬዳዋ ቴክኒክና ሙያ እና በሳቢያን ሃይስኩል በመምህርነት እና በምክትል ርዕሰ መምህርትነት
    – በድሬዳዋ ት/ቢሮ በእቅድ ዝግጅትና አስተባባሪነት
    – የድሬዳዋ አስተዳደር የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ እንዲሁም ህይወታቸው እስካለፈበት እለት ድረስ በእንባ ጠባቂ ተቋም የመረጃ እና የግንኙነት ዳይሬክሬት ዳይሬክተር በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩ ቱጉና ታታሪ ሴት ነበር፡፡
    የድሬደዋ አስተዳደር በወ/ሮ ስንዱ ከበደ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለ ቤተሰቧቿ ለወዳጅ ዘመዶችዋና ለስራ ባልደረቦችዋ መጽናናትን ይመኛል ፡፡