የአፍሪካዊያንና የመላው ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ምሳሌ የሆነውን፤ የኢትዮጵያዊያን ጀግኖች የአሸናፊነትና አልበገር ባይነት መንፈስ ለመስበር፤ እንዲሁም ኢትዮጵያን ደካማ፣ የተበታተነችና ሉአላዊነቷን የተነጠቀች ሀገር ለማድረግ፤ አሸባሪው የህወሓት ቡድን እና ጀሌዎቹ ምዕራባውያን ሀገራት ግልፅ ጦርነት ከከፈቱብን ሰንብተዋል።

    መላው የድሬዳዋ ህዝብ እና የአስተዳደራችን አመራሮች፤ እንደ ጀግና አባቶቹ “ተከተሉኝ” ብሎ ኢትዮጵያን ሊያድን ወደ ጦር ሜዳ ያቀናውን መሪያችንን ጥሪ ተቀብለን፤ የምንችል በግንባር ቀሪዎቹ ደጀን ሆነን፤ የአድዋን ድል በመድገም አዲስ ታሪክ ለመስራት፤ ሌት እና ቀን በአንድነት መትጋት ይኖርብናል። እመኑኝ… እኛ ኢትዮጵያዊያን ለሀገራችን የሚጠበቅብንን ዋጋ በመክፈል፤ ታሪክ ከሚያደንቃቸው የጀግና ልጆች መካከል አንዱ ሆነን፤ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በክብር መዝገብ ላይ በወርቅ ቀለም የምናትምበት ጊዜ ቅርብ ነው።