የድሬደዋ ትራፊክ ፖሊስ ፣የታክሲ አሽከርካሪዎች እና ባለንብረቶች በጋር በመሆን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ በማሰባሰብ ድጋፍ አደረጉ።
በድጋፍ መርህ ግብሩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድ/ዳ/አስ ከንቲባ አቶ ከድር ጅዋር የታክሲ አሽከርካሪዎች እና ባለንብረቶች የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናቸው ለማሳየት ለሰሩት ለሌሎች አርያነት ያለው የድጋፍ ተግባር ምስጋናቸውን አቅርበው ከድሬዳዋ የሽብር ቡድኖችና ተግባራትን ብሎም ቁሻሻን ለማስወገድ በተጀመረው ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ ተሳትፎና ድጋፋችሁ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል::
የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽነር አለሙ መግራ በበኩላቸው የድሬዳዋ ከታክሲ አሽከርካሪዎች ጋር በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ተካሂደው የነበሩ ውይይቶች ስኬታማ እንደነበሩ ተናግረው የታክሲ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች የሀገራችን ያለችበት ሁኔታ በመረዳት ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት በገንዘብ እና ደም በመለገስ ያሳያችሁት ወገናዊነት ከተባበርን የማንሸገራቸው ችግሮች እንዳሌሉ መሳያ ነው ካሉ በሃላ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቀርበዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የትራፊክ ቁጥጥር ዳሪክተር ኢ/ር ይህነው ሽፈራው እና የሌሊት ታክስ አሽከርካሪዎች ማህበር ሊ/መንበር ወጣት ቃልክዳን ፀሀይ ስለ ተደረገው ድጋፍ ዋናኛ አላማና የተገኘውን የድጋፍ መጠን በተመለከት ገለፃና ንግግር አድርገዋል::
በአጠቃላይ በድጋፉ የድ/ዳ ትራፊክ ፖሊስ ፣የታክሲ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች በጋራ ያሰባሰቡት ሁለት ሚሊዮን ሁለት ሺ አምስት መቶ ብር እንዲሁም በድሬደዋ ሳቢያን ፖሊስ ካንፕና አካባቢው የወጣቶች መረዳጃ እድር አርባ ስድስት ሺ ብር ለመከላኪያ ሰራዊት ድጋፍ የተደረገ ሲሄን በሽብር ቡድኑ ለተፈናቀሉና ለተጎዱ ወገኖች የሚውል ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሰበሰቡ አልባሳትና ጫማዎችም እንዲሁ ድጋፍ ተደርጓል።
ምንጭ ፦ ድሬ ፖሊስ


