በድሬዳዋ የሚከበረው የ16ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን አከባበር ዝግጅት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ዛሃራ ሁመድ የበዓሉ አስተግባሪ ኮሚቲ እንዲሁም በአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ሐርቢ ቡህ የሚመራው የበዓሉ ዝግጅት ንዑሳን ኮሚቴዎች በዝግጁቱ ላይ ተወያይተዋል።
በግምገማውም የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ሐርቢ ቡህ በዝግጅት ምእራፉ የተከናወኑ ተግባራት ሲያስረዱ ለእንግዶችን የመስተናገዱና የማረፊያ ቦታ ማመቻቸት፣ የትራንስፖርት ምችችት እንዲሁም ያለምንም የፀጥታ ችግር በአሉ እንዲከበር ከፀጥታ አካላት በተጨማሪ የከተማ ታክሲ አገልግሎት ሰጪዋች እንዲሁም ማህበረሰቡ አሁን ሀገራችን ያለችበትን ሁኔታ ተከትሎ በትጋት ሰላማቸውን ለማስጠበቅ እየሰሩ በመሆናቸው በበዓሉ ያለምንም ፀጥታ ችግር ይከበራል ብለዋል።
የከተማዋን የበዓሉ ድምቀትና ዝግጅት አስመልክተው ለተወያዮች ያስረዱት የአስተዳደሩ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ በበኩላቸው በከተማዋ ዋና ዋና ቦታዋች የቢልቦርድ፣ፖስተሮች የመስቀልና የድሬደዋ መገለጫ የሆነውን ባቡር ባለፊት አመታት በነበረው ስርአት ከቦታው የተነሳውን ባቡር ወደ ነበረበት ለገሀር አደባባይ የመመለስ እንዲሁም l love Dire በመስራት በአሉን ለማክበር ዝግጁ መሆኑን ጠቁመዋል።
የ16ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን አከባበር አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት እንድሁም በድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ የሚመራው ኮሙቴ የቀሩ የበአሉ ስራዋች እስከ ነገ ድረስ እንዲያጠናቅቁ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ዛሃራ ሁመድ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።


