መላው የድሬደዋ አስተዳደር ነዋሪዎች እና ተቋማት እንዲሁም ድርጅቶች በሙሉ ህዳር 29/2014 ‹‹ወንድማማችነት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት›› በሚል መሪ ቃል ለ16ኛ ጊዜ በአስተዳደራችን በሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በዓል የድሬደዋ እሴት የሆነውን የፍቅር የአብሮነትና የመቻቻል ባህላችንን ወደ ድሬዳዋ ለሚመጡ እንግዶች በፍጹም ወንድማማችነትና ስሜት በመቀበል ከተማችን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በወንድማማችነትና በፍቅር የሚኖሩባት ትንሿ ኢትዮጵያ መሆኑኗን እንድታሳዩና በዓሉ የተሳካ እንዲሆን የበኩላችሁን ሁሉ እንድታደደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን ፡፡ ለበአሉ ድምቀትም ሁሉም ነዋሪና ተቋማት እንዲሁም ድርጅቶች የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በየበራፋቸሁ እንዲሰቅሉ አስተዳደሩ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡