የድሬዳዋ አስተዳደር ውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን ለታላቁ የህዳሴ ግድብ የ1 ሚሊዮን ብር ቦንድ ለአስተዳደሩ አበርክቷል።

    በመርሀ ግብሩ የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እንደተናገሩት አስተዳደሩ ለወራት ያክል የሕዳሴ ግድብ ዋንጫ ከሐረሪ ክልል በመረከብ የገቢ ማሰባሰቡ ስራ እየተከናወነ መቆየቱን በመጠቆም እንደ ሀገር ህግን ከማስከበር ጎን ለጎን በራሳችን ጉልበትና ገንዘብ ለመገንባት ያቀድነው ትልቁ ኘሮጀክት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተጠናቆ ለሀገራችን ልምላሜ እና ብልፅግና እንዲውል የመንግስትና የግል ተቋማት አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
    የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የባለስልጣኑ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሀርቢ ቡህ የተቋሙ ሰራተኞች ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ለሦስተኛ ጊዜ ድጋፍ በማድረጋቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
    በዛሬ እለት ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ለሦስተኛ ጊዜ የ1ሚሊዮን ብር የቦንድ ግዥ በመፈፀም ለአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጁሀር ያስረከቡት የውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ መሀመድ ሙሴ በርክክቡ ላይ እንደተናገሩት የኘሮጀክቱ መጠናቀቅ የውሀ አገልግሎት አሰጣጡ ሳይቆራረጥ እንዲደርስ ያደርጋል ብለዋል።