16ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል በድሬዳዋ መከበር ጀመረ

    አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 16ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል በድሬዳዋ ከተማ መከበር ጀመረ።
    በዓሉ ‹‹ወንድማማችነት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት›› በሚል መሪ ቃል ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡
    ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ ብሄር ብሄረስቦች ዛሬ ጠዋት በውብቷ ድሬዳዋ በ ባቡር ከድሬዳዋ እስከ ሽንሌ ከተማ በመጓዝ ጥሩ ትዝታ አስቀሪቷል
    በአሁኑ ሰዓትም ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተወከሉ ብሔር ብሔረሰቦች በባህላዊ አልባሳት አሸብርቀው የተለያዩ ባህላዊ ትርዒቶችን እያሳዩ ነው፡፡
    የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዘቦች ህገ-መንግስታዊ እኩልነት እና ኅበረ ብሔራዊ አንድነት ማሳያ የሆነው ይህ በዓል በየዓመቱ ህዳር 29 ቀን በተለያዩ ሰነ ስርዓቶች በድምቀት ይከበራል፡፡