በድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ አዘጋጅነት <<ለኢትዮጵያ ሰላም ይስፈን፤ በአሸባሪው ሕወኃት ቡድን በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀም ጥቃት ይብቃ!>> በሚል መሪ ቃል የፀረ ፆታዊ ቀን አስመልክቶ ህብረተሰቡን ያሳተፈ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በምድር ባቡር አደባባይ በአሁን ሰዓት እየተካሄደ ይገኛል።
በሰላማዊ ሰልፉ ታዳሚዎች የተለያዩ መፈክሮች የተያዙ ሲሆን የሴቶች፣ ህፃናትና የልጃገረዶችን ጥቃት ለመከላከልና ለማስወገድ ሁላችንም ሀላፊነታችንን እንወጣ፣ ፆታ ተኮር ጥቃት ይብቃ ፣ዝም አንልም፣ የሴቶች ጥቃትን እንደ ጦር መሳሪያ መጠቀም ይብቃ የሚሉ እና እንዲሁም #NO MORE!!!!! የሚሉ መፈክሮች ይዘው ወተዋል።
በሰልፍ ስነ-ስርአቱ የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጆሀርና ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የመከላከያ ሚኒስትር የሴቶችና ህፆናት ዘርፍ ዳሪክቶሪት ዳሪክተር ሜጀር ጀነራል ጥሩዩ አሰፋ ታድመዋል።


