የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሐላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ እንደገለፁት በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጲያውያን እና ትውልደ ኢትዮጲያውን ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የምዕራብያውያን መንግስታት ጫናን ለመቋቋም በውጭ እያደረጉ ያለውን ጥረት እውቅና ለመስጠት መንግስት ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ መሆኑን ገልፀዋል ወደ ከተማችን የሚገቡ እንግዶቹን ለመቀበል በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
በዝግጁቱ ላይ የባንክ ተቋማት ፣የግሉ ዘርፍ እንዲሁም የሲቪክ በጎ አድራጎት ማህበራት የሚሳተፉ ሲሆን በቀጣይ በአስተዳደሩ የልማት ስራዎች ላይም የዲያስፖራው ማህበረሰብ በማሳተፍ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ በከተማችን የተለያዩ መድረኮች እንደሚዘጋጁ ተገልፃል፡፡
በድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት የዲያስፖራ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አቤል አሸብር እንደገለፁት ፕሮግራሙን ለማዘጋጀት ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን ኮሚቴ በማዋቀር ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጸው ሲምፖሲየም ፣ የሙዚቃ ኮንሰርት ፣ ጥናታዊ ፅሁፎች ፣ኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሁም ለመከላከያ ሰራዊታችን እና ለተፈናቀሉት ወገኖች ድጋፍ እና የደም ልገሳ እንዲሁም ስፖርታዊ ውድድሮች የሚካሄዱ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
ሀገራዊ ጥሪውን አስመልክቶ ወደ ከተማችን የሚገቡ የድሬዳዋ ዳያስፖራ ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ በከተማችን ያሉ የኢንቨስትመንት እና የልማት አማራጮችን በመለየት ለከተማች እድገት አሻራቸውን የሚያሳርፉበት በዓል በመሆኑ የድሬዳዋ አስተዳደር የሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመቀናጀት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተገልፃል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዓብይ አህመድ ባቀረቡት ጥሪ መሰረት ወደ ድሬዳዋ አስተዳደር አንድ ሺህ የሚጠጉ የድሬዳዋ ዲያስፖራ ማህበረሰብ በበዓሉ ላይ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል
ምንጭ ፦ንግድ እንዱስትሪና ኢንቬስትመንት ቢሮ


