ሁሉን አቀፍ የሴቶች ተሣትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ስኬታማ እንዲሆኑ የሙያ ተቋማት የትምህርት መስኮች መጠናከር እንዳለባቸው ተገለፀ፡፡
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የትምህርትና ስነ- ባህሪ ኮሌጅ ከትምህርት እቅድና ስራ አመራር ትምህርት ክፍል ጋር በመተባበር የድሬዳዋ ኢትዮ-ጣሊያ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 45 ሴት መምህራንን አሰልጥነዋል፡፡
በስልጠናው ወቅት የተገኙት ፕሮፌሰር ገመቹ አበራ እንዳስገነዘቡ ሴት ሙሁራን ሚና ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው በአገሪቱ ሴቶችን በሁሉም መስክ ለማብቃት የሚደረጉ ጥረቶች ከቤተሰብ መጀመር እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
ለአስር ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ለሰልጣኞች ሰርተፊኬት በመስጠት በተሳካ መልኩ ተጠናቋል፡፡


