ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ ወደ ከተማችን ለሚገቡ ዲያስፖራ ማህበረሰብን ለማስተናገድ ከሆቴል ባለቤቶችና ባለሙያዎች ጋር የምክክር መድረክ ማካሄዱን የድሬዳዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡

    የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ ኢንዱስትሪና አንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ሐላፊ አቶ አብዲ ሙክታር በምክክር መድረኩ ላይ እንደገለፁት የዲያስፖራ ማህበረሰብን ለመቀበል ከተማችን የተለያዩ እንቅስቃሴዎችና እያደረገች መሆኑን ገልፀው የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንግዶቹን በመቀበልና የቆይታ ግዜያቸውን ለማራዘም የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል መስራት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡
    ወደ ከተማችን የሚመጡ እንግዶቹን ለመቀበል በከተማችን ውስጥ ከሚገኙ የሆቴል ባለቤቶች ጋር በመነጋገር 30% የአገልግሎት ቅናሽ ለማድረግ የተስማሙ ሲሆን አንድ ሆቴል ደግሞ 50% ቅናሽ በማድረግ እንግዶችን ለማስተናገድ ዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡
    ሀገራዊ ጥሪን ተከትሎ ወደ ከተማችን የድሬዳዋ የሚገቡት አንድ ሺህ የሚጠጉ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አስተዳደሩ ባዘጋጀው የተለያዩ ፕሮግራሞች ላይ እንደሚሳተፉ የተገለፀ ሲሆን የቆይታ ግዜያቸውን ለማራዘም የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንግዶችን ከወትሮ በተለየ መንገድ ማስተናገድ እንዳለባቸው ተገልጿል።