በአስተዳደሩ ለሚገኙ አመራሮች በድህረ ጦርነት ስትራቴጂ ዙሪያ ስልጠና መስጠት የተጀመረ ሲሆን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር ጦርነቱ የህዝብ አንድነትና ጥንካሬን የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።
ለሰልጣኞች የተዘጋጁ ሁለት ሰነዶች ዘርዘር ያለ ማብራሪያ የሰጡት የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በጦርነቱ የተገኘው ድል የግለሰብ ወይም የቡድን ብቻ ሳይሆን የህዝብ መሆኑን አስረድተዋል።
በከፍተኛ አመራሮች የተጀመረው ይህ ስልጠናና ውይይት ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።


