የእየሱስ ክርስቶስ ልደት(የገና)በዓል ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር ለማስቻል ፖሊስ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን ገለፀ ፡፡

    በዓሉን በማስመልከት የድሬዳዋ ፖሊስ የህ/ግንኙነት ዋና ክፍል ሀላፊ ም/ኢ/ር ባንታለም ግርማ ለተለያዩ የሚድያ አካላት መግለጫ ሰተዋል።
    ሃላፊው በመግለጫቸው በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩ ታላላቅ በአላት መካከል እንደ የእየሱስ ከርስቶስ ልደት (የገና) በአል እንደመሆኑ ለበአሉ ፍፁም ሰላማዊነት የድሬዳዋ ፖሊስ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን ነው የገለፁት ፡፡
    ም/ኢ/ር ባንታለም ግርማ እንዳስታወቁት በእዚሁ በዓል ምንም አይነት የወንጀል ተግባርና የትራፊክ አደጋ ሳይከሰት እንዲከበር ለማስቻልና ሊደርስ የሚችል የእሳት ቃጠሎን መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት በመስጠትና እቅድ በማውጣት ቅድመ ዝግጅት መደርጉን ተናግረው አሁን ላይ ሙሉ የሰው ሀይልን በግልፅ በስውር ጥበቃ በመመደብና በማሰማራት እንዲሁም ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በተቀናጀ መልኩ ወደ ስራ መግባቱን የተናገሩት፡፡
    ከወትሮ በተለየ መልኩ በበአሉ ዋዜማና በበአል እለት በግብይት እና በመዝናኛ ስፍራዎች የሰዎች ቁጥርና እንቅስቃሴ እንደሚጨምር ታሳቢ በማድረግ በገበያና በመዝናኛ ስፍራዎች እንዲሁም በከተማው የተለያዩ አካባቢዎች የትራፊክ አደጋ እንዳይከሰትና ወንጀሎች እንዳይፈፀም ትኩረት ሰቶ የሚሰራም ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
    የጠ/ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድን ጥሪ ተከትሎ ወደ ሀገር ቤት በመገንባት ወደ ድሬዳዋ የመጡ ዲያስፖራዎችና የድሬዳዋ ወዳጃች በድሬዳዋ የሚያደረጉት ቆይታ ፍፁም ሰላማዊም እንዲሆን ፖሊስ ትኩረት ሰቶ እየሰራ መሆኑንም ሃላፊው አያይዘው ገልፀዋል ።
    ማህበረሰቡ በተለይ በግብይት ወቅት ከተለያዩ የወንጀል ድርጊት፣ ስርቆቶችና ሀሰተኛ የብር ኖቶች ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ ያሳሰቡት ም/ኢ/ር ባንታለም ግርማ መላው መህበረሰብ ፖሊስ ለሚያከናውናቸው ተግባራት እያደረገ ያለውን እገዛና ትብብር ይበልጥ በእዚህ በአልም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅረበው ለመላ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ በአሉ የሰላምና የደስታ በዓል እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል ፡፡
    ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ ጥቆማና መረጃ ለመስጠት በ025-111-16-00/025-111-52-11 በመደወል 24 ሰአት አገልግሎት ማግኘት እንዲሚችልም በመግለጫው ተመላክቷል::