የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በዓሉ የሰላም፣የደስታ እንዲሆንላችሁ ሲሉ መልካም ምኞታቸውን የተመኙ ሲሆን!
አገራችን ኢትዮጵያ በህብረብሄራዊ አንድነቷ ለአፍታም ቢሆን የማይደራደሩ ልጆች እንዳላት ለዓለም ያሳየችበት ታላቅ ጊዜ ላይ ነን፡፡ ከሀገራቸው በፊት እራሳቸውን የሚያስቀድሙ ጀግኖች ልጆች እናት ነች፡፡ ይህን የዘንድሮ የገና በዓል ስናከብርም በታላቅ መሰረትነት ላይ የተገነባውን አንድነታችንን በማጠናከርና ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት የምናደርገውን ድጋፍ አጠናክረን በማስቀጠል መሆን ይኖርበታል፡፡
በወንድማማችነት ያገኘነውን ድል አጠናክረን ለማስቀጠል አሁንም ይህን አንድነታችንና አብሮነታችንን ማጠናከር ይኖርብናል፡፡
መልካም የገና በዓል


