አስተዳደሩ ባዘጋጀው ስምፖዚይም እንዲገኙ ተጋብዘዋል።

    በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ የሚደርገውን ኢፍትሃዊ ጫና በመቀልበስ፣ የሀገራችንን ጥቅም ማስጠበቅ ይቻል ዘንድ እና ሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችንን ለማጠናከር በመላው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አዲሱን የፈረንጆች ዓመት መሰረት በማድረግ ወደ ሀገር ቤት እንድትመጡ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር አብይ አህመድ በኩል የእናት አገር ጥሪ በተደረገላችሁ መሰረት በሚካሄደው ስኬታማ የዳያስፖራ ማህበረሰብ ንቅናቄ ላይ ለመሳተፍ እና ድጋፍም ለማድረግ እንደመጣችሁ የሚታወቅ ነው፡፡
    በመሆኑም የድሬደዋ አስተዳደር የዲያስፖራ ማህበረሰብ ንቅናቄውን በደመቀ እና በተሳካ ሁኔታ በማክበር ፤ ቆይታችሁም የተመቻቸ ለማድረግ የተለያዩ ዝግጅቶች እየተከናወኑ ይገኛል ፡፡ ስለዚህ ከመርሀ-ግብሮቻችን አንዱ የሆነው ለዲያስፖራው የኢንቨስትመንት ተሣትፎን የሚያበረታቱ ፣ አማራጮችና አዋጪ የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ ያተኮረ የሲምፖዚየም ፕሮግራም በጥር 07 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፤00 ሰዓት ጀምሮ በብሎሰም ሆቴል አዳራሽ የሚካሄድ ሲሆን በእለቱ በተጠቀሰው ሰዓት እና ቦታ እንድትገኙ በክብር እንጋብዛለን፡፡